ማስታወቂያ :ለዲላ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በሙሉ

"የጠራ የሳይንስና ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራሞች እና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕድገት፣ልማትና ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ፣ እና በቁልፍ የውጤት አመላካች ዙሪያና በዲላ ዩኒቨርስቲ የዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ለመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የተዘጋጀ ሥልጠና ከመጋቢት 13-14 ዓ.ም ድረስ በሦስቱም ግቢዎች ይሰጣል። በመሆኑም በዕለቱ በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ፣ በኦዳያኣ ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽና በሆስፒታል ግቢ በዋናው ቤተመጻሕፍት የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ ባለመቅረት እንዲገኝ እናሳስባለን።
የሥልጠና ሰነዶችን ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም መስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል።https://t.me/dprd9/139
ማሳሰቢያ:
ኮቪድ-19ኝን በጋራ እንድንከላከል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ-ማስክ ማድረግ አይርሱ።