የሀገር በቀል እውቀት ቅድመ ማስጠንቀቂያ የምርምር ማረጋገጫ ወርክ ሾኘ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ::

ዲ ዩ ሐምሌ 10/2013 (ህ.ግ) አለም ከተፈጠረች አንስቶ አባቶቻችን የባህላዊ እውቀትን ጠብቀው አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ ማቆየታቸውን የገለፁልን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ተወካይና የአስ/ተማ/አገልግሎት ም/ኘሬዚዳንት ዶ/ር ዲዊት ሀዬሶ በአለማችን በርካታ ችግሮች ስከሰቱ በምድር ያለውን ምርምር አልፈው በህዋ ስመራመሩ የቆዩት ዛሬ ላይ ለሀገር በቀል ባህላዊ እውቀት ትልቅ እውቅና በመስጠት ላይ ናቸው ብለውናል::
አክለውም ዶ/ር ዳዊት አሁን ላይ የምታየው ስልጣኔ መነሻው ባህላዊ እውቀት በመሆኑ ሁለቱንም በማቀናጀት የህዝቡን ኑሮ ማሻሻልና ጤናን መጠበቅ ይገባል ብለዋል::
አቶ ምትኩ ታምሩ የደቡብ ብሔር÷ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ በ14 ወረዳዎች የሚገኙ ሲሆን ይህ ማህበረሰብ በበርካታ መለኪያዎች ወደ ኃላ የቀረ ከመሆኑም ባለፈ በተደጋጋሚ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰትበት በመሆኑ ሁኔታውን ለማሻሻል መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በርካታ ሰራዎችን እየሰሩ መምጣታቸውን ተናግረው በነዚህም ተግባራት ሀገር በቀል እውቀትን አካቶ የመስራቱ ጉድለት ሰፊ እንደነበረ ተናግረዋል::
አቶ ምትኩ አክለው አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት ከአንጋፋው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ቢሮአችን ብዙ ስራዎችን ለመስራት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ሀገር በቀል በጥናት የተረጋገጡ ቅድመ ማሰጠንቀቂያ ሰርዓቶችን ከመንግሰት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጋር አካቶ በቀጣይ የሁለቱን ግንኙነት ተጠቅመን አካባቢው ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን መመከት እንችላለን ብለዋል::
የዚህ ኘሮጀክት አስተባባሪና ተመራማሪ ዶ/ር አብዮት ለገሰ በዚህ ምርምር ላይ 8 አባላት የተሳተፉ ሲሆን ይህም ኘሮጀክት በምዕራብ ኦሞ÷ በደቡብ ኦሞ÷ በሱርማ÷ ደሰነችና ጋቶሚ እና ሀመር አከባቢ ለሚገኙ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መሆኑን ገልፀዋል:: ሀገር በቀል ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዕውቀትን ከዘመናዊ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እውቀት ጋር በማዛመድ የህብረተሰብን ህይወትና ደህንነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለውናል::
በውይይቱ ላይ ያነጋገርናቸው ከዳሰነች የመጡት አቶ ኡያ ሎኮታሜ የአከባቢው የሀገር ሽማንግሌ ሲሆኑ የዚህ አይነት ውይይት ጠቃሚ በመሆኑ ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል ብለውናል::