የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥ ጽ/ቤት ለጽ/ቤት ኃላፊዎችና ለቡድን መሪዎች በመልካም አስተዳደር እና በተቋማዊ ለውጥ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡

ዲ/ዩ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ሁሉም ስኬቶች የሚጀምሩት ከአስተሳሰብ ነው ያሉን የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ በቂ ሀብት ቢኖር እንኳን ሰው በአስተሳሰብ ካልተቃኘና በውስጣዊ ስሜቱ መስራት ካልቻለ ውጤት ሊያመጣ አይችልም ብለው ይህ ስልጠና በአመለካከትና በክህሎት የበለፀገ ማህበረሰብ እንዲኖረን ትልቅ እገዛ አለው ብለውናል፡፡
ዶ/ር ዳዊት አክለው ተራማጅ በሆነ ወቅት ላይ ሆነን ተራማጅ አስተሳሰብ ካልያዝን በርካቶች አልፈውን ስለሚሄዱ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀትና አስተሳሰብ መቃኘትና መተግበር ያስፈልጋል ብለውናል፡፡
ሠራተኞች በJEJ የተነሣ ወደ አዳዲስ ክፍሎች የገቡ በመሆኑ እነኝህን ሰራተኞች የማነቃቃት ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለፁልን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክተር አቶ ይመኑ ዳካ አሁን ባሉበት አካባቢ እንዴት መልመድ እንዳለባቸውና የተሰጣቸውን ኃላፊነቶች በአግባቡ እንዲወጡ ያስችል ዘንድ ለቅርብ ተጠሪዎችና ኃላፊዎች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነው ያሉት አቶ ይመኑ በቀጣይ በተቋምና በጽ/ቤቶች ደረጃ ለሚመቻቹ ስልጠናዎች ትልቅ ግብዓት የተገኘበት ስልጠና ነው ብለውናል፡፡
ከተሳታፊዎች አቶ ቢንያም ሽፈራው ከHIV መከላከልና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት እና አቶ ሲሳይ ወርቁ ከማህበረሰብ አገልግሎት በበኩላቸው ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀና በእጅጉ አስፈላጊ እንደነበር ተናግረው ይህ ስልጠና በቀጣይም ወደታችኛው ክፍል መድረስ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡