በዲላ ከተማ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነፃ ሕክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል::

ዲ.ዩ. ነሐሴ 29 (2013) ህ/ግ/ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች በዲላ ከተማ በተለምዶ ማዞሪያ በሚባል አካባቢ ነፃ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዶ/ር ተሰፋዬ ጉግሳ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የጥራትና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክተር እና የግብረ-ሃይሉ አሰተባባሪ ነፃ ሕክምናው ሪፈራል ሆስፒታሉ ከሚሰጣቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው በዛሬው ዕለት በዲላ ከተማ እየተካሄደ ያለው ፕሮግራምም በጤና ጥበቃ የጥራት ለውጥ ቁጥጥር ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ እንደሆነ ገልፀዋል::
ዶ/ር ተሰፋዬ አክለው በቀጣይ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎቸ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ገልፀው ማህበረሰቡም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቀድሞ በማወቅ እንዲጠነቀቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የህክምና አገልግሎቱን ስጠቀሙ ያገኘናቸው አቶ ለማ ተፈራ አገልግሎቱ እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልፀው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ይሄን አገልግሎት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል::
ባጠቃላይ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከ500 በላይ የምርመራ አገልግሎት ካገኙት ውሰጥ 200 የስካር እና የደም ግፊት በሽታ ምልክቶች ያሳዩ ሲሆን 27 የሚሆኑት ደግሞ ተጨማሪ ምርመራ ስለሚያስፈልጋቸው ወደ ሪፌራል ሆሰፒታል መላካቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ተላላፊ ያልሆኑትን በሽታዎች ቀድሞ በመመርመር÷ በመለየት እና በመጠንቀቅ ጤናዎን ያረጋግጡ!
.......
ትኩስና ወቅታዊ መረጃ እንዲደርስዎ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይጎብኙ፣
......
ዌብሳይት: www.du.edu.et
ቴሌግራም: https://t.me/dprd9
Dilla University
University of the Green Land!