የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል በ2013 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ህ/ክ ጤና ቢሮ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባስመዘገበው ውጤት የላቀ አፈጻፀም እውቅና ተሰጠው፡፡

ዲ.ዩ. ታህሳስ 02/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ) የጤና ተቋማት ዋና ዓላማቸው በሽታን መከላከልና መቆጣጠር መሆኑን የተረዳው የዲላ ዩኒቨርስቲ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ሆስፒታሉ በላቀ ውጤት አፈፃፀም በክልል ጤና ቢሮ መሰጠቱ የተቋማችንን ሠራተኞች ብሎም ክፍሎችን ለላቀ ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል የህክምናና ተግባር ስልጠና ዋና ዳሬክተር ዶክተር ደረጀ ዳንኤል ይህን እውቅና ለሠራተኛው ለማሳወቅና ተነሳሽነቱን ለማጎልበት ሲነር ማናጂመንት አባላት ልዩ መድረክ ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡
ሆስፒታላችን የህክምና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 16 ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በነኝህ ግዜያት በዚህ በሽታ የታከመና አገልግሎት ያገኘ 6000 (ስድስት ሺህ) የሚጠጋ ተገልጋይ ብቻ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ደረጀ በአሁኑ ሰዓት 1835 ሰዎች የኤች አይ ቪ መድኃኒት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ኩኡ በበኩላቸው ሪፌራል ሆስፒታላችን ያገኝው ውጤት አስደሳች እንደሆነ ገልፀው ይህን ውጤት አስጠብቆና አሻሽሎ የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ሠራተኛው በተሻለ ሞራልና ትጋት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት ምክትል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሣሙኤል ዳርጊ ይህ በአሁኑ ሰዓት ለሆስፒታሉ የተሰጠው የላቀ አፈፃፀምና እውቅና ሪፌራል ሆስፒታሉ ኤች አይ ቪን በመከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ላሳየው ትጋት መሆኑን ገልጸው ዛሬ የተገኘው ውጤት በሠራተኛው ትጋትና በአመራሩ ቁርጠኝነት መሆኑን አቶ ሣሙኤል ተናግረዋል፡፡