ምርምር ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ ‘‘ቴክኖ ሰርቭ’’ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የሳይንስ ሳምንት መርሃግብር ተጠናቀቀ
Dilla University receives educational simulator and machine donations
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርደ በዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ከተቋሙ ከፍተኛ አመራር ጋር ተወያየ
ዜና ትንታኔ ዲ.ዩ፡- ህዳር 03/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ በዩኒቨርሲቲው የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ዝርዝር ውይይት አካሄደ፡፡ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢዋ እና የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የስራ አመራር ቦርዱ አባላት በውይይቱ ተገኝተዋል፡፡ በእለቱ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአራቱ የምክትል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤቶች፣ በህክማና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲሁም የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት እና በስሩ ያሉ ባለ ብዙ ዘርፍ ፅ/ቤቶች ባለፈው አመት ያከናወኗቸው ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበዋል፡፡ በዝርዝር ሪፖርቶቹ በአመቱ የታቀዱ፣ የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም በአፈፃፀም የተገኙ እምርታዎች እና ጉድለቶች ከተወሰዱ መፍትሄዎች ጋር በዝርዝር ተዳስሰዋል፡፡ የበጀት ዓመቱን የመማር ማስተማር ተግባራት ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍቃዱ ወ/ማርያም በዓመቱ
የ‹ሲ.ቲ ስካን› ማሽን ስራ መጀመሩ ተገለጸ
ዲ.ዩ፡- ጥቅምት 15/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገዛው የ‹ሲ.ቲ ስካን› ማሽን ስራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ሆስፒታሉ የህክምና ስራዎቹን ለማሳለጥ እና ተደራሽነት ለማስፋት ከሚጠቀመው ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች አንዱ መሆኑን ነዉ የተገለጸው። በዩኒቨርሲቲው የሕክምና እና ሳይንስ ኮሌጅ እና ጠቅላላ ሆስፒታል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ምጽዋ ሩፎ ሆስፒታሉ ከጌዴኦ ዞን፣ ኦሮሚያ እና ሲዳማ አጎራባች ክልሎች ለሚመጡ ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሕብረተሰብ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል፡፡ ለሕብረተሰቡ ከሚሰጣቸው የህክምና አገልግቶች በተጨማሪ ሆስፒታሉ በጤና ዘርፍ ተማሪዎችን በተለያዩ የሕክምና ሙያ መስኮች ተቀብሎ እያስተማረ እና እያሰለጠነ እንደሚገኝም ዶ/ር ምፅዋ ገልፀዋል፡፡ እሳቸው አክለውም አዲስ የተገዛው ‹ሲ.ቲ ስካን› በዚህ ሳምንት ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ጠቅላላ ሆስፒታ