ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል

ዲዩ፤ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ያረጁ ቡናዎችን በመጎንደል፣በመንቀልና በምትካቸው አዳዲስ በምርምር ውጤታማነታቸው የተረጋገጠና የተሻለ ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞችን በማፍላትና ለአርሶ አደሩ የማዳረስ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የምር/ቴ/ሽ/ም/ፕ ዶ/ር ፍሬ ሕይወት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

የነጥብ የሥራ ምዘናናደረጃ አወሳሰን ዜደ (JEG) ድልደላ

ዝርዝሩን ለማየት ይህንን ይጫኑ(የነጥብ የሥራ ምዘናናደረጃ አወሳሰን ዜደ (JEG) ድልደላ )

ለዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በሙሉ፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ደብዳቤ ማስታወቂያ መሠረት የአስተዳደር ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች አወዳድሮ ድልደላ ያደርጋል፡፡ሠራተኞች የሚወዳደሩበት የሥራ መደብ ካላቸው ዝግጅት እንዲያጠኑ በማሰብ የውድድር ፎርም የሚሞላው ከታህሳስ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሚወጣ ዝርዝር ፕሮግራም መሠረት ይሆናል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል መሰረተ ትምህርት የአጭር ጊዜ ስልጠና እየተሰጠ ነው

ዲዩ፤ ነሐሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ከኮምፒውቲንግ እና እንፎርማቲክስ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ሁለት ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች መሠረታዊ የኮምፒውተር ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
የኮምፒውተር መሠረታዊ ዕውቀት(Computer Basics)፣ የበይነ መረብ አገልግሎቶች አጠቃቀም (The Internet, cloud services and world wide web)፣ የአገልግሎት ሰጪ መተግበሪያ ፕሮግራሞች አጠቃቀም(Productivity Programmes)፣ የዲጂታል አኗኗር (Digital lifestyles)፣ የግል መረጃ ደህንነት አጠባበቅ(Computer security and privacy) በዲጂታል መሠረተ ትምህርት (Digital Literacy) ስልጠና እየተዳሰሱ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡

Pages