የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማሽን ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ

በአጠቃቀሙ ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ዲዩ፤ መስከረም 28 ቀን 2013 ዓ/ም፣ (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ያስመጣው የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማሽን በጥቅምት ወር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ዶ/ር ፍራኦል ንፍታሌም የተግባር ስልጠና እና ትምህርት ዋና ዳይሬክተር እና የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅና በሪፈራል ሆስፒታል ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ ገለጹ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ጊዜያት ለኮቪድ-19 ምርመራ ከጌዴኦ ዞን ናሙና ወደ ሀዋሳ ይላክ የነበረውን ለማስቀረት መመርመሪያ ማሽን መግዛቱን አስታውሰው በሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ አገልግሎት ለመስጠት የጤና ባለሙያዎችን ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ዶ/ር ፍራኦል አስታወቀዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአረንጓዴ አሻራ ቀን

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአረንጓዴ አሻራ ቀን ከ10 ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች ተተከሉ
ዲዩ፤ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የአረንጓዴ ቀንን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ የዕፅዋት ጥበቃና ኢኮ-ቱሪዝም ማዕከል ችግኝ ተከለዋል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በታሪካዊው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የተቋሙ አመራሮች፣ ሠራተኞችና ተማሪዎች በነቂስ ወጥተው በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል፡፡
በተያዘው ዓመት ለአካባቢ ጥበቃ ልዩ ትኩረት በመስጠት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው ጥሪ ሁሉንም ያነቃና አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ተናግረዋል፡፡
የበረሀማነት መስፋፋትን ለመግታትና ብዝሀ ህይወትን ለመጠበቅ ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት መሠጠቱ አስፈላጊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማኅበረሰቡ ችግኝ ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ባህል ማዳበር ይኖርበታል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Pages