ዲላ ዩኒቨርሲቲ በክረምት የበጎ-ፈቃድ ሥራ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አከናወነ፡፡

ዲ.ዩ. ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት በማስተላለፍ ንግግራቸውን የጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የበጎ ፈቃድ ሥራው በያዝነው ክረምት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በመመደብ በወናጎ ወረዳ 7 ቤቶች እንዲሁም በዲላ ከተማ 6 ቤቶች በድምሩ 13 ቤቶችን በ15 ቀናት ውስጥ ለተቸገሩ ቤተሰቦች ገንብቶ በማስረከብ በኢኮኖሚ አቅማቸው የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ታስቦ የተጀመረ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡  ለመርሃ ግብሩ መሳካት ድጋፍ ያደረጉትንና በዕለቱም ተገኝተው ሥራውን በጋራ ያስጀመሩትን የዲላ ከተማ እና የወናጎ ወረዳ አስተዳደር ካቢኔ አባላትን አመስግነው ቤት ለሚታደስላቸው ቤተሰቦችም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ችሮታው አያይዘውም እንዲህ ዓይነት ተግባር በቀጣይ አመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መዝጊያ ስነ-ስርዓት አከናወነ፡፡

ዲ.ዩ ጳጉሜ 03/2013 ዓ.ም (ህ.ግ) በቀጣይ ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን እንተክላለን ያሉት በፕሮግራሙ የተገኙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ እንደ ሀገር “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል በዚህ ዓመት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲው በንቃት ሲሳተፍ መቆየቱን ገልፀው በዚህም 121 ሺህ ምግብ ነክ ያልሆኑ፣ 100 ቀርከሀ፣ 8040 ምግብ ነክ የሆኑ እና ተቋሙ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የሚገኘው ምርጥ የቡና ዘር 247 ሺህ በአጠቃላይ ከ376,000 በላይ ችግኞችን በዩኒቨርሲቲው እና አካባቢው መተከሉን ተናግረዋል፡፡

ጌዴኦ እና አካባቢው አረንጓዴ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም የበለጠ አልምተን ለሀገራችን አረንጓዴ አሻራ የማኖሩን ስራ በእጅጉ እናግዛለን ያሉት ዶ/ር ችሮታው ለቀጣይ ዓመት የሚተከሉ ችግኞችን የማፍላት ሥራ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተቀጠሩ የካምፓስ ፖሊስ አባላት ሲሰጥ የቆየው ሙያዊ ስልጠና ተጠናቀቀ::

ዲ.ዩ. ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም. (ህ.ግ.) በሀገራችን ባለፉት ጊዜያት በተለያዩ ተቋማት የሰላም ችግር እንደነበረ የተናገሩት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ኘሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ኘሬዝዳንት ተወካይ በነዚህ ጊዜያት ተቋማችን ሰላማዊ ሆኖ የቆዬ ሲሆን ይህን ሰላም በቀጣይ እንደምታስቀጥሉ እተማመናለሁ ብለዋል::
በዚህ አጭር ግዜ የአካል ብቃት÷ ወታደራዊ ሰልፍ እና ዲስፕሊን በማሰልጠን ተልቅ እገዛ ያደረጉትን የፌዴራል ፖልሶችን አመሰግነው የዚህ አይነቱ ስልጠና በቀጣይ ለአጠቃላይ አባላቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል::

በዲላ ከተማ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነፃ ሕክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል::

ዲ.ዩ. ነሐሴ 29 (2013) ህ/ግ/ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች በዲላ ከተማ በተለምዶ ማዞሪያ በሚባል አካባቢ ነፃ ህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ዶ/ር ተሰፋዬ ጉግሳ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል የጥራትና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክተር እና የግብረ-ሃይሉ አሰተባባሪ ነፃ ሕክምናው ሪፈራል ሆስፒታሉ ከሚሰጣቸው የማህበረሰብ አገልግሎቶች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው በዛሬው ዕለት በዲላ ከተማ እየተካሄደ ያለው ፕሮግራምም በጤና ጥበቃ የጥራት ለውጥ ቁጥጥር ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ እንደሆነ ገልፀዋል::
ዶ/ር ተሰፋዬ አክለው በቀጣይ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎቸ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ገልፀው ማህበረሰቡም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቀድሞ በማወቅ እንዲጠነቀቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቨርሚ ኮምፖስት የአፈር ማዳበርያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ በወናጎ እና አባያ ወረዳ ለሚገኙ ሞዴል አርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ።

ዲ.ዩ. ነሐሴ 28 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ.) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ከግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ጋር በመተባበር በቨርሚ ኮምፖስት የአፈር ማዳበሪያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ወናጎ እና አባያ ወረዳ ለሚገኙ ሞዴል አርሶ አደሮች ስልጠና ሰጠ።
ሞዴል አርሶ አደሮች ከስልጠናው በኃላ በራሳቸው ማሳ ላይ ኮምፖስቱን ማምረት እንዲችሉ የተለያዩ የተግባር ስልጠናዎች መሰጠቱን የገለጹት የማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቴር አቶ ክብሩ አለሙ ቴክኖሎጂው ቀለል ያለ በመሆኑ ሁሉም በአካባቢው ለማምረት የሚያስችል ሲሆን በአፈር ለምነት ምክንያት ተፈጥሮ የነበረውን የምርታማነት ችግር የመቀረፍ ዕድሉ ከፍ ያለ እንደሆነም ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በቡታጅራ ባዘጋጀው ፎረም ለዶ/ር ሰላማዊት አየለ በስራ ዘመን በአመራር ብቃት የላቀ የአመራር ዘርፍ ሽልማት ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (ህ.ግ.) በቡታጅራ በተካሄደው የደቡብ ክልል ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የጤና ሴክተር የ2013 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም የምክክር መድረክ ላይ በተደረገው የእውቅና መድረክ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፈራል ሆስፒታል ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰላማዊት አየለ በስራ ዘመናቸው በላቀ አመራር ዘርፍ በአመራር ብቃት እና በትልቅ ትጋት ቁርጠኝነት ለብዙዎች አርአያ በመሆን ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት የክልሉ ጤና ቢሮ እውቅናና ሰርተፍኬት ክርስታል ዋንጫ መሸለማቸው ተገለፀ፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ከሠላጣኝ ተማሪ ወላጆች ጋር ውይይትና ጉብኝት አደረገ፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 27/2013 ዓ.ም. (ህ.ግ) ለአንድ ሀገር ዕድገት ሳይንስና ትክኖሎጂ ዋነኛዉ ምሰሶ ነዉ ያሉት አቶ ተካኝ ታደሰ የSTEM ማዕከል ዳይሬክተር ማዕከሉ ለሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጠቁ ዜጎችን ለማፍራት የበኩሉን አስተዋዕፆ እያደረገ ባለዉ ጥረት በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ 8 ወረዳዎች እና 4 የከተማ አስተዳደሮች የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ፈጠራ ዝንባሌ÷ በትምህርት ቤታቸው ባላቸው የፈጠራ ክበብ ተሳትፎ እና በሳይንስ እና ትክኖሎጂ ውጤታቸው ተወዳድረው ያሸነፉትን በማዕከሉ በክረምት ለ2 ወር ስልጠና እና ትምህርት እየተሰጠ እንዳለ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተቀጠሩ የካምፓስ ፖሊስ አባላት ስልጠና ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ. ነሐሴ 25 (2013 ዓ.ም.) (ህ.ግ.) በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ አንጋፋ ተቋማት መካከል አንዱ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ዳዊት ሀይሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተ/አ/ም/ፕረዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ተቋሙ ከ5,500 በላይ የአስተዳደርና አካዳሚክ ሠራተኞች የያዘ÷ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች በተለያዩ በመደበኛና በተከታታይ ፕሮግራሞች እንደሚያስተምር ጠቅሰው በቀጣይ 10 ዓመታት በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት በሀገራችን ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም ለመሆን ራዕይ ነድፎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ይሄን ትልቅ ራዕይ ለማሳካት እናንተ አዲስ የተቀጠራችሁ የካምፓስ ፖሊስ አባላት በትክክለኛ ስነ- ምግባር ጠንክራችሁ በመስራት የበኩላችሁን ጥረት እንዲታደርጉ ይገባል በማለት ዶ/ር ዳዊት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ በአመራርና አሰራር ስርዓት ነባራዊ ሁኔታ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ልምድ ልውውጥ አደረገ፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም (ህ.ግ) ይህ ተቋም የጋራ እንደመሆኑ መልካም ተሞክሮ ካላቸው ተቋማት ልምድ በመቀመር ተቋማችንን ማሸጋገር የአመራሩ ቁርጠኛ ሀሳብ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ወደድንም ጠላንም በአሁኑ ሰዓት አለም በፈጣን ሁኔታ እየተቀየረች ሀገራትና ተቋማት እየተቀየሩ ባሉበት ወቅት ላይ ተቋማችን የለውጥ ምህዋር ውስጥ በመግባት ለውጡን ማፍጠን ግድ ነው ብለውናል፡፡
የበላይ አመራሩና ሠራተኛው የለውጥ መንገዱን ለማስቀጠል ቁርጠኛ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የሚሰራበትን አሰራር በመቀየር በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር መዘርጋትና ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

Pages