የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቡና ልማት ላይ ስልጠና ለመስጠት ለግብርና ባለሙያዎች አቀባበል አደረገ፡፡

ዲዩ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከኢሊባቡር ዞን ለተወጣጡ 39 የግብርና ባለሙያዎች በቡና ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና ለመስጠት ለሰልጣኞች አቀባበል አድርጓል፡፡
በአቀባበሉ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በምርምር ላይ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን በአርሶአደሩ ዙሪያ መልካም ልምዶችን ለማስፋትና የቡና ሴክተሩ ራሱን ችሎ በተሻለ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ይህን መሰል ስልጠና መሰጠቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች በካምፓስ ሕይወት አኗኗር ጥበብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ::

ዲ ዩ ሐምሌ 3/2013(ህ.ግ.) ወደ ዩኒቨርስቲያችን ተመድበው የመጡትን ተማሪዎች ተቋሙም ሆነ ክፍሎች ለመቀበል ያደረጉትን ዝግጅት በመግለፅ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኤች አይ ቪ መ/መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ሽፈራዉ ወደ መማር ማስተማር ስራ ከመገባቱ በፊት የካምፓስ ህይወት የመምራትን ጥበብ ግንዛቤ እየተዝናኑ እውቀት እንዲቀስሙ ታሰቦ የተዘጋጀ መደረክ ነው ብለዋል::
በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ግንዛቤ ካስጨበጡት መካከል በካውስልንግ የረዥም አመታት ልምድ ያላቸው የስነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር ታረቀኝ ታደሰ ተማሪዎች በተቋም ቆይታቸው ወቅት እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን ከሕይወት ተሞክሮአቸውም አካፍለዋል::

ለ2013 አዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

ዲ/ዩ ሐምሌ 2/2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት የፍሬሽማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዲን ዶ/ር አስናቀ ይማም ዲላ ዩኒቨርሲቲ እናንተን ለመቀበል ማናቸውንም ዝግጅት አጠናቆ የቆየ በመሆኑ በቆይታችሁ የሰመረ ጊዜ ይኖራችኋል ብለዋል፡፡

ማስታወቂያ :ለዲላ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በሙሉ

"የጠራ የሳይንስና ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ፕሮግራሞች እና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕድገት፣ልማትና ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ በዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ፣ እና በቁልፍ የውጤት አመላካች ዙሪያና በዲላ ዩኒቨርስቲ የዐሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ለመምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች የተዘጋጀ ሥልጠና ከመጋቢት 13-14 ዓ.ም ድረስ በሦስቱም ግቢዎች ይሰጣል። በመሆኑም በዕለቱ በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ፣ በኦዳያኣ ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽና በሆስፒታል ግቢ በዋናው ቤተመጻሕፍት የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ ባለመቅረት እንዲገኝ እናሳስባለን።

ከቡና ገለፈት የሚዘጋጅ ሥነ ህይወታዊ የአፈር ማዳበሪያ ፕሮጀክት ሥራ ጀመረ

ዲየ፤ ታህሣሥ 08 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተሰራውና በጌድኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ቱማታ ጪርቻና በአባያ ወረዳ የተጀመረው ከቡና ገለፈት የሚዘጋጅ ሥነ ህይወታዊ የአፈር ማዳበሪያ (ቨርሚ ኮምፖስ) ፕሮጀክት ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዶ ፕሮጀክቶ በይፋ ሥራ ጀመረ፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በቡና ምርታቸው ከታወቁት ሀገራት አንዷ ስትሆን ቡና ተረፈ ምርት ላይ ሳታውል መቆየተዋን ያነሱት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ይህ አካባቢን እየበከለ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየውን የቡና ገለፈት በአሁኑ ሰዓት በቨርሚ ኮምፖስ አገልግሎት ላይ እንዲውል መደረጉ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ አገልግሎት ፋይዳ ያላቸውን ሦስት ፕሮጀክቶችን አስመረቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎትን ታሳቢ በማድረግ ካከናወናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ተኮር የሬዲዮ ጣቢያ ኤፍ.ኤም 89.0፣ የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማዕከልና የወተት ላሞች እርባታና ቴክኖሎጂ ጣቢያ ይገኙበታል፡፡ በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ተገኝነተው ፕሮጀክቶችን የመረቁት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ምስራቅ መኮንን የማህበረሰብ ሬዲዮው ለማህበረሰቡ ከማስተማርና ግንዛቤን ከመፍጠር አንጻር ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ ማህበረሰቡ የሚያዳምጥ ብቻ ሳይሆን የሚሳተፍበት እንዲሆን መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አክለውም የኮቪድ-19 መመርመሪያ ማዕከልም ሆነ የወተት ላሞች እርባታና ቴክኖሎጂ ጣቢያው ለህብረተሰቡ ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው በማት ገልጸዋል፡፡ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ሽፈራው ቦጋለ በበኩላቸው የሬዲዮ ጣቢያ መከፈቱ የአካበቢው ማህበረሰብ መረጃ ለማግኘት ያለውን አማራጭ የ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል

ዲዩ፤ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ያረጁ ቡናዎችን በመጎንደል፣በመንቀልና በምትካቸው አዳዲስ በምርምር ውጤታማነታቸው የተረጋገጠና የተሻለ ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞችን በማፍላትና ለአርሶ አደሩ የማዳረስ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ የምር/ቴ/ሽ/ም/ፕ ዶ/ር ፍሬ ሕይወት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

Pages