Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

Uncategorized

ዲ.ዩ፤ የካቲት 19/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማሕበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ለስምንት የሥነ-ዜጋና ሥነ ምግባር የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒዩተር በስጦታ አበርክቷል።
ኢዮብ ቀለመወርቅ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማሕበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን፤ እንደገለጹት የሥነ -ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የነበረባቸውን የኮምፒዩተር ችግር በመረዳት የትምህርት ክፍሉ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር የኔነሽ ተመስገን በስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ በሄዱበት ጊዜ በጎ አድራጊ ኢትዮያዊያን በማስተባበር ስምንት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ገዝተው ለተማሪዎች አበርክተዋል።
ዶ/ር ኢዮብ አክለውም፤ ሀሳቡን አመንጭተው አቅደው ወደ ተግባር ለቀየሩት ዶ/ር የኔነሽና ሀሳባቸውን ተቀብለው ለበጎ አላማ እጃቸውን ለዘረጉት ለወ/ሮ ገነት አስራት እና አቶ ታምራት አወይቱ ምስጋና አቅርበዋል።
የኔነሽ ተመስገን (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት ክፍል መምህርት፤ ተማሪዎች ፕሮጀክቶችን እና ምርምሮችን ለመስራት የኮምፒዩተር ችግር እንዳለባቸው በመረዳት በስራ አጋጣሚ ወደ ሀገረ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት ያገኟቸውን በጎ አድራጊ የሆኑትን ወ/ሮ ገነት አስራት እና አቶ ታምራት አወይቱን በማነጋገር ስምንት ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን በማምጣት ለተማሪዎች በስጦታ እንዳበረከቱላቸው ገልጸዋል።
አቶ መሳይ ፍቅሩ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፤ በስጦታ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የምናስተምራቸው ተማሪዎች የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ጫናዎችን ተቋቁመው የነገ ህልማቸውን እውን ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ አስታውሰው፤ አስተዋይና ሙያውን የሚያከብር አስተማሪ ለተማሪዎቹ የቀለም ትምህርት መስጠት ብቻ ሳይሆን ተማሪዎቹ ያለባቸውን የግልና የጋራ ችግር ቀርቦ በመረዳት ችግሮችን ለመፍታት የበኩሉን አስተዋፅኦ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።
አቶ መሳይ አክለውም፤ ሀሳቡን በማንሳት ወደ ተግባር እንዲቀየር ላበቁት ዶክተር የኔነሽ ተመስገን እንዲሁም ሀብታቸውን ለወገናቸው ቀና ተግባር እንዲውል በማሰብ ኮምፒዩተሩን ገዝተው ለላኩት ወ/ሮ ገነት አስራት እና አቶ ታምራት አወይቱ እንዲሁም ኮምፒተሩ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባና ለተማሪዎች እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ዶክተር ኢዮብ ቀለመወርቅና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ምስጋናና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ስጦታው ከተበረከተላቸው ተማሪዎች መካከል አስናቀ ጋቢሶ እና ታደለ ቱማቶ በሰጡን አስተያየት፤ የተበረከተላቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተር የነበራቸውን የኮምፒዩተር ችግር በመቅረፍ የቀረውን የትምህርት ጊዜቸውን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚያግዛቸውና የምርምር ስራቸውን በቀላሉ ለመከወን እንደሚያስችላቸው ገልጸው፤ ሀሳቡን ላመነጩ መምህርታቸው እንዲሁም ድጋፉን ላደረጉ ግለሰቦች፣ ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ለኮሌጁ ኃላፊዎች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *