Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ ሚያዝያ 24/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለወናጎ የሥነ-ህዝብ ማዕከል ሠራተኞች በመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
አቶ ትዝአለኝ ተስፋ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማህበረሰብ አገልግሎት እይታ በርካታ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተው፤ በወናጎ የስነ ህዝብ እና ጤና ቅኝት የምርምር ማዕከል የሚሰራው ስራ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል።
በሥነ ህዝብ ማዕከሉ የማህበረሰቡን የሚመለከቱ መረጃዎች መሰብሰብ መቻሉ በዋናነት የማህበረሰቡን ችግር ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈታ መነሻ እንደሚሆን አቶ ትዛለኝ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
ምስጋኑ ለገሰ (ዶ/ር)፣ የምርምር፣ ህትመት፣ ስነ ምግባርና ስርፀት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ውጤታማ የሆነ ስራ እንደሃገር ለመስራት የሚወሰኑ ውሳኔዎችና የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች ዳታን መሰረት አድርገው መሆኑን አስረድተው እያንዳዱ ዳታ ሰብሳቢ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ በጣም የተለየ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ አበበ እጅጉ፣ የወናጎ ወረዳ አስተዳዳሪ በተለያዩ ጉዳዮች ማህበረሰቡ ውስጥ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ችግሮች በጋራ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጥናት አስደግፎ መረጃዎችን በማሰባሰብ ራሱን አስችሎ መረጃ የሚያሰባስቡ ሠራተኞችን በማሰልጠን ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ውጤትም የሚያስገኝ መሆኑን አንስተዋል።
በስልጠናው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ አካሉ፣ ማዕከሉ ሲመሰረት በወናጎ እና አካባቢው በተለይ በጤናና ስነ ህዝብ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ በአገር አቀፍም ደረጃ በእዚህ ዙሪያ ላይ ለሚሰሩ ስራዎች የሞዴል መሆን የሚችል ማዕከል መመሰረት ያስችላል የሚል ሃሳብ ተይዞ እንደነበር አስታውሰው ማዕከሉን ስራ ለማስጀመር የመጀመሪያው ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር አለማየሁ፤ አክለው ዩኒቨርሲቲው ስራዎችን የሚመራ ተቋም እንደመሆኑ የሚያስፈልጉትን የሰው ኃይል የማሟላት፣ ግብዓት የማቅረብ ኃላፊነቱን ወስዶ እየሰራ ያለ መሆኑን አንስተው፤ መረጃ ሰብሳቢ ባለሙያዎች መረጃን በጥራት የመሰብሰብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት አቶ አልአዛር ባህሩ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስነ ህዝብ እና ጤና ክትትል ምርምር ማዕከል ዳታ ማናጀር፤ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ማደራጀት በተመለከተ፤
ዶ/ር መኮንን ብርሃኔ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ እና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ት/ክፍል መምህር፣ በመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችና መገልገያ መሳሪያዎች ዙሪያ እንዲሁም አቶ ሀብታሙ እንዳሻው፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የወናጎ ጤናና ስነ ህዝብ ክትትል ምርምር ማዕከል ኃላፊ፣ የማዕከሉን ራዕይና ተልዕኮ የስራ እንቅስቃሴ እና ስለ ጤናና ስነ ህዝብ ክትትል ምርምር ማዕከል አጠቃላይ ገለጻ አድርገዋል።
ስልጠናውን ከወሰዱ ሰልጣኞች መካከል አቶ አብርሃም ቱጂ፣ መረጃዎችን እንዴት በስርዓት መሰብሰብ እንዳለባቸውና ዳታውን እንዴት ወደ ኮምፒውተር ማስገባት እንደሚቻል ዕውቀትና ክህሎት እንዳገኙበት ገልጸውልናል።
ለተከታታይ ሦስት ቀናት የተሰጠውን ስልጠና 20 የመረጃ ሥራ አመራር ሰራተኞች መከታተላቸው ታውቋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et