Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ህዳር 30/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለ18ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን “መቼም የትም በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል” በሚል መሪ ሃሳብ ለተከታታይ 6 ቀናት የሚከበረው የነጭ ሪቫን ቀንን በማስመልከት ለተቋሙ ሴት መምህራን ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል።

ወ/ሮ አለሚቱ ብርሃኑ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር፤ 40 ለሚሆኑ የተቋሙ ሴት መምህራን የስራ ፈጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው፤ ሰልጣኝ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ሥራ ፈጣሪ ለማድረግ እንዲሁም ራሳቸውንም የቢዝነስ አስተሳሰብ ይዘው የተሻለ ነገር እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የስራ ፈጠራ ክህሎት እንዴት እንደሚያዳብር ግንዛቤ የተገኘበት፤ እራሳቸውን ያዩበት፣ ተማሪዎቻቸው ላይ ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።

ወ/ሮ ጽጌረዳ ወ/ሚካኤል፣ የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት አሰልጣኝና የቢዝነስ አማካሪ በበኩላቸው፤ የሥራ ፈጠራ ስልጠና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ስልጠና መሆኑንና ገልጸው በተመሳሳይ በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች እየተሰጠ ያለ ስልጠና መሆኑን አስገንዝበዋል። በስልጠናው ላይ መምህራኑ በሙሉ አቅም ተሳትፎ እንደነበራቸውም አውስተዋል።

ወ/ሮ ወንጌል የሸዋልዑል እና አቶ ተመስገን አብርሃ የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ማዕከል አሰልጣኝ በበኩላቸው፤ የስልጠናው አላማ ሰዎች የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ የባህሪ ለውጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን አስረድተው ሰዎችን የሥራ ፈጣሪነት አቅማቸውን የሚለኩበት እንደሆነም አስገንዝበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፣ ዶ/ር አለማየሁ አካሉ በበኩላቸው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ አሁን በሀገሪቱ ከሚገኙ 15 የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑንና የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ልየታቸው ከተሰጣቸው አምስት መሠረታዊ ነገሮች አንዱ የስራ ፈጣሪነት እሳቤን ማጎልበት መሆኑን አስረድተዋል።

ዶ/ር አለማየሁ አክለውም፤ ከኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖርን ትስስር በማጠናከር ኢንዱስትሪዎችን የሚፈጥርና ችግሮቻቸውን የሚፈታ፣ አዳዲስ የቢዝነስ አስተሳሰብ ያላቸውን ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን አስተማሪዎችንም ጭምር መፍጠር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል የስፖርት ሳይንስ መምህርት እና የትምህርት ጥራት ም/ዳይሬክተር ናርዶስ ኤልያስ እና የሀይድሮሊክስና ውሃ ምህንድስና ት/ክፍል መምህርት እንዲሁም የፍሬሽ ማን ፕሮግራም አስተባባሪ ቤተልሄም በለጠ፤ ወደ ቢዝነስ ለመግባት ምን አይነት ባህሪ ሊኖረን ይገባል የሚለውን የተገነዘብንበት፣ የራስን ገቢ ማመንጨት የምንችልባቸው ነገሮች ምንድን ናቸው የሚለውን የፈተሽንበት ነው ሲሉ ይገልጻሉ። ስልጠናውን በትክክል ለተሳተፉ ሰልጣኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡