Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 3/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ከኢትዮጵያ ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች ማሕበር (Women in coffee Ethiopia) ጋር በመተባበር በቡና ምርት ጥራት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በስልጠናው የመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና አምራች በሆኑት ይርጋ ጨፌ፣ አማሮ፣ ሲዳማና ጉጂ መካከል የሚገኝ እንደመሆኑ መጠን ላለፉት አምስት ዓመታት ለቡና ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም በማደራጀት፣ ምርምሮችን በመስራት፣ ምርጥ ዘር የቡና ችግኝ በማፍላት ለአካባቢው ማሕበረሰብ በማደል፣ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችንና ተዛማጅ ስራዎች ሲከውን መቆየቱን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፤ ይህ ስልጠና ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች ላይ ትኩረት በማድረግ በቡና ምርት ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለሚያበረክቱ እናቶች እንዲሰጥ በማሰብ ላዘጋጁት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም እና የኢትዮጵያ ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች ማሕበር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ ቡና ቀአካባቢው ብሎም በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመው፤ ዩኒቨርስቲው ይህንን በመረዳት በቡና ልማት ዘርፍ ያረጁ የቡና ተክሎችን በየዓመቱ ከ5 መቶ ሺህ በላይ በምርምር የለሙ የቡና ችግኞች በነፃ ለአከባቢው አርሶ አደሮች በማደል እንዲሁም የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በመስራት የቡና ምርታማነትን እና ጥራትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በቡና ምርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸውን ሴት አርሶ አደሮች በስልጠናው የራሳቸውን የህይወት ልምድ እንዲያጋሩ በማድረግ ወቅቱ የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት እንዲያገኑ መደረጉ ስልጠናውን ልዩ እንደሚያደርገው ዶ/ር ሀብታሙ ገልጸዋል።
ወ/ሮ ሳራ ይርጋ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባልና የኢትዮጵያ ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች ማሕበር (Women in Coffee Ethiopia) ፕሬዚዳንት፤ በኢትዮጵያ አብዛኛው የቡና ልማት ስራ በሴቶች ጉልበት የሚሸፈን መሆኑን ጥናቶች እንደሚያሳዩ አስረድተው፤ ሴቶች ባላቸው የላቀ ተሳትፎ ልክ ተጠቃሚ ካለመሆናቸው ባለፈ በቡና ጥራት ላይ ጭምር የራሱን ጫና እንደሚያሳድር ገልጸዋል።
በዚህም የሴቶችን አቅም መገንባት በቡና ምርት ጥራት ብሎም አቅርቦት ላይ ድርሻው የጎላ መሆኑን በመድረኩ የጋራ መግባባት በመፍጠር ሴቶችና ቤተሰቦቻቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ ጥሩ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉን አያይዘው ገልጸዋል።
አለሙ ዳሳ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ በቡና ልማት ሴቶች ባላቸው ተሳትፎ ልክ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል የግንዛቤ እጥረትና የተሳሳተ የፆታ አተያይ እንዲሁም የገበያ ትስስር ችግር መሆኑን አንስተዋል። እነዚህን ችግሮች ለማቃለል በምርት አሰባሰብ፣ ዝግጅትና በድህረ ምርት ዙሪያ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ጥራት ያለው ቡና ለገበያ በማቅረብ ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ስልጠና መሰጠቱን አስገንዝበዋል።
ስልጠናውን የወሰዱት ሴት ቡና አልሚ ገበሬዎች በሰጡን አስተያየት በቡና ልማት ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸው የግልና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት ለማሻሻል እንደሚያግዛቸው ጠቅሰው ዩኒቨርስቲው መሰል ስልጠናዎችን በማዘጋጀቱ መደሰታቸውን ነግረውናል።
ሥልጠናው ከጌዴኦ ዞን፣ ከአጎራባች ክልል ሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ እና ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ለተውጣጡ 70 ሴቶችና ለ አራት የግብርና ባለሙያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በዘርፉ ባለሙያዎች መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *