Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሰኔ 14/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ከሰኔ 14 -21/2016 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የሚሰጠውን አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር )፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት፤ በዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መንግስት እንደ ሀገር የትምህርት ዘርፉን ለመቀየርና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የሚያደርገው የሪፎርም አካል እንደሆነ ገልጸው፤ ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ አብይ እና ንዑሳን ግብረ ኃይሎችን አቋቁሞ ፈተናውን በአግባቡ በመስጠት መንግስት እያደረገ ያለውን የትምህርት ሪፎርም እንዲሁም የዲጅታል አቅምን ለማሳደግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ ዶ/ር ታምራት ገለፃ፤ በዩኒቨርሲቲው በመደበኝነት ለሚፈተኑ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ለማስቻል የተለያዩ የሞዴል ፈተናዎችን ከመስጠት ባለፈ የኮምፒውተር ክህሎት እና የስነ ልቦና ዝግጅቶች ስልጠና በየኮሌጁ እንዲወስዱ መደረጉን ታውቋል።
ወ/ሮ የሺወርቅ ቲሊንቲ፣ በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ተማሪዎች ልማት ባለሙያ በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተናውን በተመለከተ ከሂደቱ ጀምሮ ከአመራሩ ጋር በቅርበት በመነጋገር ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላትና አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በዛሬው ዕለት የመውጫ ፈተናው መጀመሩን ተናግረዋል።
ወ/ሮ የሺወርቅ አያይዘውም፤ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ከሰኔ 14 ጀምሮ የሚካሄደውን ይህን የመውጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲው በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ከጥበቃ ጀምሮ እስከ ፌደራል ፖሊስ ድረስ ያሉ የጸጥታ ኃላፊዎች የፈተናው ሂደት ከደንብ ጥሰት ነፃ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ተገቢውን ክትትል በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በዩኒቨርሲቲው የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክተር መ/ር በቀለ ወርቁ በበኩላቸው፤ የመውጫ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ ለፈተናው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ የኮምፒተር፣ የኔትወርክና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ ተሟልተው በዛሬው እለት በማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የመውጫ ፈተናው መጀመሩን ገልጸው፤ ለዚህም በአይ ሲቲ በኩል ለፈተናው በኦዳያኣ ግቢ 16 ላብራቶሪዎች እንዲሁም በቀድሞ ዋና ግቢ ላይ 5 ላብራቶሪዎች በአጠቅላይ 21 የመፈተኛ ክፍሎች ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
ዳይሬክተሩ አያይዘውም፤ በቀጣይ ቀናት ይህን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በተለይም ደግሞ ከግል የትምህርት ተቋማት የሚመጡ ተፈታኞች የመለያ ስም (Username ) እና የይለፍ ቃላቸውን ( password) በደንብ አውቀውና በትክክልም ሊስታቸው እዚህ ሲስተም ላይ መኖሩን ቀድመው አረጋግጠው መምጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
አስናቀ ይማም (ዶ/ር )፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራል በበኩላቸው፤ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዚህ የመውጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ወደ 2738 የሚጠጉ እጩ ተመራቂዎች በፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸው፤ ከእነዚህም ውስጥ 2,387 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተመራቂዎች ሲሆኑ የተቀሩት 68 ተማሪዎች፣ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ፤ 283 ተማሪዎች ደግሞ ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዚህ ቀደም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ዘንድሮ ዳግም የሚፈተኑ ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው እስከ ሰኔ 19/2016 የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ አጠቃላይ ተማሪዎች ዲላ ዩኒቨርሲቲ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *