Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News Uncategorized

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 21/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት አዘጋጅነት ለዲላ እና ዳማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል።

አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር፤ ዩኒቨርስቲው ለአካባቢው ማሕበረሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንዱ የሆነው ሙያዊ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከኮምፒውተር መምህራን ጋር በመተባበር በዲላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 112 ተማሪዎች እንዲሁም በዳማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 65 ተማሪዎች በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው በቀጣይም የትምህርት ጥራት ለማሻሻልና የተማሪዎችን ውጤት ከፍ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ዘርፈ ብዙ ስራዎች ለማከናወን እቅድ መያዙን ገልጸዋል።

አቶ ዮናስ ያደለ፣ የዲላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቤታቸው ድረስ ባለሙያዎችን በማስተባበር ተማሪዎች ዘመኑ የሚፈልገውን መሰረታዊ ክህሎት እንዲይዙና ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁ የሚረዳ ስልጠና በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ስልጠናውን ከሰጡ ባለሙያዎች መካከል መምህር ሳሙኤል ጉደታ እና መምህርት ህይወት ወናጎ፤ ስልጠናው በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት እንዲሁም የበይነ መረብ አጠቃቀምን ያካተተ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስልጠናውን የወሰዱት ተማሪዎች በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ በመሆናቸው ከወዲሁ ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁ እገዛ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ትርሐስ መላኩ እና ዘመኑ ሳሙኤል በሰጡን አስተያየት፤ በዘርፉ ሰፊ እውቀትና ልምድ ባለቸው መምህራን በመሰጠቱ ጥሩ መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን አስገንዝበዋል።

ስልጠናው 7 ሙያዊ በጎ ፍቃደኛ የኮምፒውተር መምህራን በማካተት በዲላ እና በዳማ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ለተከታታይ 15 ቀናት በመሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎትና የበይነመረብ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ታውቋል።

ዲላ፤

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et

Telegram:https://t.me/dprd9

website: https://www.du.edu.et

Email: https://www.pirdir@du.edu.et