የካቲት 28/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ) ፦ በቡና ዘርፍ ላይ አበረታች ውጤት ለማምጣት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ በመተባበር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚችሉ የገለጹት “የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ለኢትዮጵያ ቡና ኢንዱስትሪ ሽግግር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ባለው 4ኛው የቡና ሲምፖዚየም ላይ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ናቸው።
በመርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፤ ቡና ለኢትዮጵያውያን የማህበራዊ እሴትን ከማጎልበት ጀምሮ በተለያየ መልኩ ከማህበረሰቡ ህይወት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው መሆኑን አንስተው፤ ሆኖም አገራችን ኢትዮጵያ ከቡና ዘርፍ ማግኘት ያለባትን ያክል ጥቅም እያገኘች አይደለም ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ዶ/ር ችሮታው አያይዘው፤ በቡና ዘርፍ ላይ አበረታች ውጤት ለማምጣት የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ በመተባበር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል አንስተዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት የትኩረት ልየታ መሰረት አካባቢው ያለውን ተፈጥሯዊ ቡና የማምረት ጸጋ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ችሮታው፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት 6 አመታት ቡና ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱን አስገንዝበዋል።
በዛሬው ዕለት የይርጋጨፌ የቡና ምርምር ማዕከል የካርታ ርክክብ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል። አሁን ለተደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በግልም ሆነ በተቋም ደረጃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበው፤ “ከተባበርን እንገነባዋለን” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሲምፖዚየሙ በፓናል ውይይት እንደቀጠለ ሲሆን፤ በመድረኩ የመንግስት አካላት፣ ተመራማሪዎች፣ ባለሃብቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.e