Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በተልዕኮ ልየታና በትኩረት አቅጣጫ መሰረት በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (University of Applied Science) ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዙሪያ ለአካዳሚክና ቴክኒክ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ስልጠናው ሁሉም የአካዳሚክ ዘርፍ እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት እና የራሳቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱበት የሚገባ ወሳኝ ስልጠና እንደሆነ ገልፀው፤ በሀገራችን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ጥናት ተካሂዶ ሰፊ ምክክሮች ሲደረጉ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በተልዕኮ ልየታ መሰረት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (UAS) በመሆኑ ትኩረት በተደረገባቸው በግብርና፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በጤና እና በመምህራን ትምህርት በስፋት ትኩረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ለሚሰራው ስራ ስልጠናው አስፈላጊ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ስልጠናው መምህራን በልየታና ትኩረት መስክ ዙሪያ ግንዛቤያቸውን ወደ አንድ ማምጣት ያለመ እና ቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የትግበራ ሰነድ በማበልፀግ፣ በማዳበርና በማጽደቅ ወደ ትግበራ ሲገባ መምህራን የላቀ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስረድተዋል።
ከአሰልጣኞች መካከል ኢዮብ ቀለመወርቅ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን፤ ይህ ስልጠና መሠረታዊ አላማው በተግባራዊ ዩኒቨርሲቲ (Applied University) ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠርና ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተግባር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ምን ምን ጉዳዮችን ማድረግ ይጠበቅብናል የሚለውን መረጃ ለማስረጽ እንደሆነ ገልጸዋል።
ካነጋገርናቸው ሰልጣኞች መካከል በኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የምግብ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህርት ሀሊማ ኢብራሂም፣ በስልጠናው በዩኒቨርሲቲ ልየታ ላይ በተለይ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተግባር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ለለውጡ እንዴት መዘጋጀት እንዳለብንና ምን ይጠበቅብናል የሚለውን ግንዛቤ የፈጠረ ነው ብለዋል።
በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የሒሳብ ትምህርት ክፍል መምህር ደረጀ ንጉሴ በበኩላቸው፤ ከስልጠናው የአፕላይድ ሳይንስ እንዴት መተግበር እንዳለብን ስትራቴጂክ ፕላኑን መረዳትና በፓርትነርሺፕ እና በኢንዱስትሪ ግንኙነት ዙሪያ የነበሩ ተግዳሮቶች ምን እንደነበሩ አሁንስ እንዴት እንተገብራለን የሚለውን በቂ እውቀትና ግንዛቤ ያገኙበት ስልጠና እንደነበር ገልጸውልናል፡፡
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et