Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጌዴኦ ዞን 8 ወረዳዎች፣ ከምዕራብ ጉጂ አባያ ወረዳ እንዲሁም ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳዎች ለተወጣጡ የኢነርጂ ባለሙያዎች በታዳሽ ኢነርጂ (ባዮ ጋዝ፣ ብሪኬትና ፀሃይ ሀይል) አማራጮች አመራረትና አጠቃቀም ዙሪያ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ውሃ ማዕድንና መስኖ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣ አቶ ተመስገን ጥላሁን፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዞናችን ላሉ ወረዳዎች እና በአጎራባች ክልሎች ለሚገኙ የኢነርጂ ባለሙያዎች የሚሰጠው ይህ ስልጠና ዩኒቨርሲቲው በዞኑ ላይ ከባለፈው አመት ወዲህ በተለይም በታዳሽ ሀይል አማራጭ ኢነርጂ ላይ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ እየሰራቸው ለሚገኙ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ባለሙያዎችን ከማብቃት እንዲሁም የተሰሩ የባዮጋዝ ግንባታዎችን ቀጣይነት እንዲኖራቸው ከማስቻል አንፃር ስልጠናው ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
አቶ ተመስገን አያይዘውም፤ ይህ ተግባር ተኮር ስልጠና ለባለሙያዎችም ሆነ ለዞኑ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፤ ባለሙያዎች ከስልጠናው በኃላ ወደ መጡበት ሲመለሱ ለህብረተሰቡ ውጤት ማስገኘትና ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ከአሰልጣኞች መካከል በዲላ ዩኒቨርሲቲው በግብርና ኮሌጅ የተፈጥሮ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህር ተመስገን ከበደ በበኩላቸው፤ ይህ በታዳሽ ኅይል ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና በተለይ በአካባቢው ላይ ያለውን ከፍተኛ የደን መጨፍጨፍ ጫና ለመቀነስ ብሎም በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ የሚደርሰውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቀነስ ግምት ውስጥ በማስገባት የተሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል።
መምህር ተመስገን አያይዘውም፤ እነዚህ ስልጠናዎች ምንም እንኳ ለባለሙያዎች ይሰጡ እንጂ ዋናው ተጠቃሚ ታች ያለው ማህበረሰብ እንደመሆኑ ህብረተሰቡ በተፈለገው መጠን ተጠቃሚ እንዲሆን ወረዳውም ይሁን ዩኒቨርሲቲው በወረዳዎች ማዕከላት ላይ እነዚህን ስልጠናዎች ለተመረጡ አርሶአደሮች በመስጠትና ድጋፎችንም በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ቢቻል ዘላቂ የሆነ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ሲሉ ተናግረዋል።
በስልጠናው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ ይህ ስልጠና በታዳሽ ሀይል በተለይም በባዮጋዝ፣ በብሪኬትና በፀሀይ ሀይል አማራጮች ላይ የተሰጠ ስልጠና እንደነበር ገልጸው፤ ይህም አካባቢው በዩኔሲኮ ጭምር በዓለም ቅርስነት ለመመዝገብ የበቃ መልክአ ምድር እንደመሆኑ ይህንን ለማስቀጠል የሚቻለው ዛፎች እንዳይቆረጡ አማራጭ ሀይሎችን መጠቀም ስንችል በመሆኑ ስልጠናው ባለሙያዎችን ከማብቃት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት እንደሆነ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ይህ ስልጠና በጌዴኦ ዞንም ሆነ በአጎራባች ክልሎች ባሉ ዞኖች ያሉ አካባቢዎችን የታዳሽ ሀይል አማራጭን ተጠቅመው ከአካባቢ ብክለት የፀዱ መሆን እንዲችሉ፣ አካባቢውንም በታዳሽ ሀይል መጥቀም እንዲችሉ የሚያደርግ ስልጠና እንደነበር አቶ ተካልኝ አያይዘው ተናግረዋል።
ስልጠናውን ሲሳተፉ ያገኘናቸው ከኮቸሬ ወረዳ አማራጭ ኢነርጂ መስሪያ ቤት የመጡት ወ/ሮ ገነት ተስፋዬ እንዲሁም ከጌዴኦ ዞን ውሃ ልማት ኢነርጂ የመጡት አቶ ብርሃኑ ከበደ፤ ስልጠናው ተግባር ተኮር ስልጠና በመሆኑ በክፍል ውስጥ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የተማሩትን በመስክ ጭምር በተግባር እንዲማሩ ያስቻለ ስልጠና እንደነበር ተናግረዋል።
አያይዘውም የተግባር ስልጠናው ከዚህ በፊት ያልነበራቸውን ዕውቀት በተለይም በብሪኬት የከሰል አመራረት ላይ ሰፊ እውቀት እና ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስቻለ እንደነበር ገልጸው፤ በቀጣይ እንዲህ ያሉ ስልጠናዎች ለህብረተሰቡም ጭምር መስጠት ቢቻል አካባቢው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስተያየት ሰጥተዋል።
በስልጠናው በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ 8 ወረዳዎች እንዲሁም ከምዕራብ ጉጂ አባያ ወረዳ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳዎች የተውጣጡ 27 የኢነርጂ ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et