Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 24/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምር ስልጠና ተቋም በአዋዳ ግብርና ምርምር መለስተኛ ማዕከል ለሰልጣኞች የመስክ ስልጠናና የልምድ ልውውጥ ማድረጉ ታውቋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምር ስልጠና ተቋም ተመራማሪና መምህር ደርቦ ጎንፋ፣ እንደ ሀገር ቡና ላይ ምርምር ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ የሆነው አዋዳ ግብርና ምርምር መለስተኛ ማዕከል ለሰልጣኞች ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ ምርት እስከ መሰብሰብ ድረስ ያለውን ሂደትና ተግባራት በመስክ ምልከታው በተግባር ሰልጣኞች እንዲገነዘቡ መደረጉን ገልጸዋል።

ሰልጣኞች ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ የየዕለት ስራቸው በመሆኑና ያገኙትን እውቀት ለአርሶአአደሮች ማሸጋገር ስላለባቸው ስልጠናው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸው፤ የማዕከሉ ባለሙያዎች ሰልጣኞችን ተቀብለው የተግባር ስልጠናና ልምድ በማጋራታቸው እንዳስደሰታቸው መምህር ደርቦ አያይዘው ገልጸዋል።

ታረቀኝ መንግስቱ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የእጽዋት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በበኩላቸው፤ በቡና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን እንደ ሀገር ቡና ላይ የሚሰሩ ተቋማት ጋር ልምድ እንዲቀስሙ ማድረግና በንድፈ ሐሳብ ደረጃ (Theoretically) ከገበዩት እውቀት ጋር በማዋሃድ ለነ ስራቸው ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አርሶአደሮች በልምድ ሲሰሩበት የቆዩበትን መንገድ ሳይንሳዊ እውቀት በማከል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ኢኮኖሚ ማገዝ እንደሚቻል ተነስቷል።

አቶ ለታ አጃማ፣ የአዋዳ የቡና ግብርና ምርምር መለስተኛ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር፤ ማዕከሉ ከተቋቋመ 24 ዓመታት አካባቢ እንደሆነ በመግለጽ፤ በአሁኑ ወቅት ከስድስት የቡና አይነቶችን በምርምር ለሀገር ያበረከተ ተቋም መሆኑን ገልጸው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞቹን ይዞ በመምጣት እየሰራን ያለውን ስራ በባለሙያዎችና በሰልጣኞች ማሳየቱ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።

በመስክ ስልጠናውና የልምድ ልውውጥ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የአራተኛው ዙር ሰልጣኞች መካከል ዘውዲቱ በቀለና ደረጄ ገረመው፤ እስከዛሬ ስለ ቡና ከምናውቀው በላይ ብዙ ነገሮችን መቅሰም መቻላቸውን በመግለፅ ለቀጣይ ስራቸው ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።

ዲላ፤

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et

Telegram:https://t.me/dprd9

website: https://www.du.edu.et

Email: https://www.pirdir@du.edu.et