Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ግንቦት 23/2016ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ አካዳሚክ ሳይንስ ጋር በመተባበር በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሽግግርና አስተዳደር ዙሪያ ያዘጋጀው ስልጠና ለዩኒቨርስቲው አመራሮች ተሰጥቷል ።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፤ በስልጠናው መዝጊያ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱን ሪፎርም ለማድረግ ያስችል ዘንድ በተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ትኩረት በማድረግ፣ ያለውን የሰው ሀብትና የአካባቢው የተፈጥሮ ፀጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ መለየት በማስፈለጉ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የተልዕኮ ልየታ ማዘጋጀቱን አውስተው፤ በተሰራው የተልዕኮ ልየታ መሰረት ዲላ ዩኒቨርሲቲ እንደ አገር ተግባራዊ ዩኒቨርሲቲ (Applied Science University) ሁኖ ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ በመሆን ግብርናን፣ ተፈጥሮ ሀብትን፣ የመምህራን ትምህርትን እና ጤናን የትኩረት መስክ አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የተልዕኮ ልየታ ማንዋል ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ እስከ ታቸኛው አመራር፣ መምህራን፣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ተረድተው ወደ ተግባር እንዲቀይሩት ጥረቶች እየተደረጉ መቆየታቸውን አስገንዝበዋል።
ስልጠናውም አመራሩ በተግባር የተደገፈ ስልጠና ወስዶ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማሕበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም የሀብት አጠቃቀምን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት ሽግግር የሚደረግበት ሁኔታ ትኩረት ተደርጎበት እንዲሰራ የሚያግዝ መሆኑን ዶ/ር ችሮታው አያይዘው ገልጸዋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፤ ተወዳዳሪና ብቁ ባለሙያዎች ለማፍራትና የትምህርት ጥራት አስጠብቆ ለማስኬድ ዩኒቨርሲቲዎች የየራሳቸውን ተልዕኮና የትኩረት አቅጣጫ መያዛቸው ጥሩ አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው፤ እንደ ተቋም ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚደረገውን ሽግግር በአግባቡ እንዲመራ፣ አዳዲስ መመሪያዎች እንዲያዘጋጁ እንዲሁም የነበሩት ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ታስቦ አዲስ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት መቋቋሙን አስረድተዋል።
አመራሩ በስልጠናው ያገኘውን እውቀትና ልምድ ከስሩ ላሉት አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች በማስተላለፍ ሽግግሩን በአግባቡና በጊዜው ወደ ተግባር ለመቀየር አስፈላጊ ርብርብ እንዲያደርግ ዶ/ር ታምራት መልእክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናውን የሰጡትን በፍቃዱ ጨመረ (ዶ/ር)፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ አመራሩ የተጀመረውን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሽግግር ተጨማሪ እውቀትና ልምድ በማግኘት ወደ ተግባር ለመቀየር የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት መሆኑን አመላክተው፤ የአፕላይድ ሳይንስ ምንነት፣ የባለድርሻ አካላት ሚና፣ የተግባር ተኮር ትምህርት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአካባቢ ፀጋ አጠቃቀም፣ የኢንዱስትሪ ትስስር፣ ኢንተርንሺፕ፣ ኤክስተርንሺፕ፣ ፕራክቲከምና ሌሎች ተዛማጅ ርእሰ ጉዳዮችን በማካተት ለተከታታይ አራት ቀናት ተግባር ተኮር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን አስገንዝበዋል።
ከሰልጣኝ አመራሮች መካከል የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክተር ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ በሰጡን አስተያየት፤ የአፕላይድ ሳይንስ ትምህርት ከንድፈ ሀሳብ ይልቅ በተግባር የሚሰጥ በመሆኑ በቂ የቤተ ሙከራዎች፣ የመስክ ትምህርት እንዲሰጥ ማስቻልና እንዲሁም ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ተጨማሪ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ህይወት ሀይሉ (ዶ/ር)፣ ከስልጠናው ያገኙት ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት ከትምህርት ክፍሎች፣ መምህራንና ሰራተኞች በማሰልጠን ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚገባውን ተግባር ተኮር ስልጠናዎች በአግባቡ በመተግበር በተሻለ ፍጥነት የአፕላይድ ሳይንስ ሽግግሩን እንዲሳካ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ገልጿል ።
ሰልጣኝ አመራሮች በይርጋለም አግሮ ኢንዲስትሪ ፓርክ በመገኘት የኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር እና ስራዎችን በተግባር ለመመልከት የሚያስችል ጉብኝት አድርገው የስልጠናው መርሃ ግብር ተጠናቋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *