ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 18/2016ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም (STEM) ማዕከል የ2016 ዓ.ም የክረምት ሠልጣኝ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም በማዘጋጀት ቅበላ ተደርጓል።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አዲሱ ፍሪጆ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር እና የምር/ቴክ/ሽ/ም/ኘሬዚዳንት ተወካይ፤ የስቴም ማዕከል ስልጠና በ2016 ዓ.ም ለክረምት መርሃ ግብር ስልጠና ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ከጌዴኦ ዞን ትምህርት ቤቶች ከ7-12ኛ ክፍል የተወጣጡ የሳይንስ ዝንባሌ ያላቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች ተቀብሎ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች ያላቸውን ዕውቀት በተግባር በተደገፈ መልኩ እንዲያዳብሩ የተዘጋጀ መሆኑን አስታውሰዋል።
ዶ/ር አለማየሁ አካሉ፤ ከጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለመጡ የሳይንስ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች እንኳን ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል በደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር አለማየሁ አክለውም ተማሪዎች ወደፊት ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም የፈጠራን ስራን ለመስራት ዛሬ ላይ ይህን ዕድል ተጠቅመው ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበው፤ ለሰልጣኞች መልካም የስልጠናና የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ ወ/ሮ መስከረም ታደሰ በበኩላቸው፤ ለክረምት ስልጠና የመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የምግብ፣ ህክምና እና የመኝታ አገልግሎት እንደተመቻቸላቸው ገልጸው፤ ተማሪዎች በሚኖራቸው ቆይታ የተቋሙን ሀብትና ንብረት በአግባቡ መያዝና መጠበቅ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
በክረምት መርሐ ግብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል የሚሰለጥኑ ከ240 በላይ ሰልጣኝ ተማሪዎች ለተከታታይ ሁለት ወራት ስልጠናውን የሚወስዱ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et