ዲ.ዩ፤ የካቲት 26/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን እና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡና ማህበር ጋር በመተባበር “የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ለኢትዮጵያ የቡና ኢንዱስትሪ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል አራተኛውን ሀገር አቀፍ የቡና ሲምፖዚየም የፊታችን ሐሙስ የካቲት 28/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል ያካሂዳል።
በመርሃ ግብሩም የቡና አልሚዎች፣ አቅራቢዎች፣ ላኪዎችና ገዥዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተገኝተው ስለ ቡና ኢንዱስትሪ ይመክራሉ፤ ምርምርን መሰረት ያደረጉ የባለድርሻ አካላት ውይይቶችም ይደረጋሉ።
በተጨማሪም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የበላይነት ለሚመራውና ትኩረቱን በቡና ምርት፣ ንግድ፣ ጣዕም እና ተያያዥ ችግሮች በሚፈቱበት መንገድ ላይ አድርጎ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ለሚገነባው የቡና ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ይከናወናል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et