Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 11/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ መርሃግብር ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የቆየው የሪሜዲያል ማጠቃለያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ዲላ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት፤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሪሜዲያል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩና በአካባቢው ባሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የሪሜዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው፤ ለፈተናው በስኬት መጠናቀቅ ሲባል ዓብይ እና ንዑስ ግበረ ሀይሎችን በማቋቋም በአገር ደረጃ መንግሥት እያደረገው ላለው የፈተና ስርቆትን የመከላከል ስራና የትምህርት ሪፎርም እንዲሁም የዲጂታል አቅምን ለማሳደግ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል
በኦንላይን ለሚሰጡ ፈተናዎች ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አቅም ገንብቶ የሪሜዲያል ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቆ በቀጣይ ለሚሰጠው አገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንዲሁም በከፊል በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ገልጸዋል።
ማቴዎስ ሀብቴ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበው ላለፋት አምስት ወራት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ተከታታይ ምዘና 30 በመቶ አጠናቀው፤ አሁን ደግሞ ቀሪውን 70 በመቶ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ፈተና በኦንላይን በተሳካ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልጸው፤ በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቸው ተከታታይ ምዘናና አሁን የወሰዱት የኦንላይን ፈተና በድምሩ ተሰልቶ 50 ከመቶና ከዛ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በቀጣይ የትምህርት ዘመን የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
መምህር መንግሥቱ ተሾመ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፍሬሽማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ እንደገለጹት፤ ከ2500 በላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲና የቢታንያ እንዲሁም የኢንፎሊንክ የግል ኮሌጅ ተማሪዎች ከሰኔ 03-11/2016 ዓ/ም ፈተና ተሰጥቶ መጠናቀቁን ተናግረው፤ ፈታኝ መምህራን፣ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ርብርብ ፈተናው በሰላምና በተሳካ ሁኔታ ሊጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።
መምህር ግርማይ ተኽላይ፣ በዩኒቨርስቲው የአይ ሲ ቲ ዳይሬክተር ተወካይ፤ የማጠቃለያ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲከወን አጠቃላይ የኮምፒዩተር፣ የኔትወርክና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ በማሟላትና በሁሉም የመፈተኛ ክፍሎች በቂ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች በመመደብ ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ችግር ሳይገጥማቸው ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ መደረጉን ገልፀው፤ በቀጣይም በኦንላይን ለሚሰጡ ፈተናዎች ጥሩ ልምድ መገኘቱን አያይዘው አንስተዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et