Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

ዲ.ዩ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ቴክኖሌጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የአግሮ ቢዝነስ ውድድር /Agro-business idea computation/ ላይ ተሳታፊ ለነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማለፍ ውድድር ተካሂዷል።

አለማየሁ አካሉ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሌጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ልዩ ረዳት በውድድር መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር፤ በዚህ ፕሮግራም ተሳትፎ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቦ 59 ተማሪዎች ተመዝግበው የህይወት ክህሎት፣ ኢንተርፕርነርሽፕ፣ የቢዝነስ ፈጠራ ሀሳቦችን እንዴት እስትራቴጂካዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀርጹ ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።

ስልጠናውን ከተሳተፉት 59 ተማሪዎች ውስጥ የተሻለ ሀሳብ ያላቸው 20 ተማሪዎች ተመርጠው በ5 ቡድን ሆነው ፕሮጀክት በጋራ መስራት የሚችሉበት እድል ተፈጥሮላቸው ለቀጣይ ውድድር ሀሳባቸውን፣ ፕሮጀቶቻቸውን እንዴት ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተጨማሪ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።

ዶ/ር አለማየሁ አክለውም፤ ይህ ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ሂደት ውስጥ አሸናፊ የሆኑ ሁለት ሁለት ፕሮጀክቶች ተመርጠው ከአራት ዩኒቨርሲቲ ስምንት ፕሮጀክቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ውድድር አድርገው ከ1-3 የወጡ አሸናፊ ሆነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚኖሩ ፈጠራ ስራዎች ውድድር ላይ እንዲሁም ከሀገር አልፎ ሌሎች ውድድሮችን እንዲያገኙ ተደርገው ሀገርን ወክለው መወዳደር የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚመቻችላቸው ገልጸዋል።

አቶ በላይ ታዬ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢንኩቤሽንና ትራንስፈር ኦፊሰር እንደገለጹት፤ ውድድሩ ተማሪዎች ከተመረቁ በኋላ የራሳቸውን ቢዝነስ እንዲሰሩ የሚረዳ ተቋም እንደሆነና ዩኒቨርሲቲያችን ካለው የተግባር ተማሪዎችን የማፍራት አላማ አንጻር ተማሪዎች የራሳቸውን የቢዝነስ ሐሳብ አፍልቆ የመስራት አቅም ከፍ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑን ገልጸዋል።

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ሆኖ ያገኘነው በዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ሁነኛው ዘሩ፣ በሰጠው አስተያየት፤ተማሪዎች ያላቸውን ሀሳብ በኢንኪውቤሽን ላይ ሰርተው ወደ ቢዚነስ ቢቀይሩና ዩኒቨርሲቲው ቴክኖሌጂ ሽግግር ውስጥ ያሉ ኢንኩቤሽን ሴንተር ላይ አፕላይ አድርገው ሀሳባቸውን ወደ ቢዝነስ መቀየር እንደሚቻል ገልጾልናል።

ዲላ፤

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et

Telegram:https://t.me/dprd9

website: https://www.du.edu.et

Email: https://www.pirdir@du.edu.et