Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 02/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል በጌዴኦ ዞን በሚገኙ ትምህርት ቤቶች፦ ገደብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ቀዲዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም አዳሜ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ኤግዚቢሽንና ፓናል ውይይት አካሂዷል።
አቶ በፈቃዱ ተድላ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ዳይሬክተር እንደገለፁት፤ የሳይንስ ኤግዚቢሽንና ፓናል ውይይቱ ዓላማ ተማሪዎች በስቴም ማዕከል ሲሰሩት የነበረውን የፈጠራ ስራ ዕድሉን ላላገኙ ተማሪዎች በየትምህርት ቤታቸው በመሄድ ግንዛቤ መፍጠር፣ ማነቃቃት እንዲሁም ተሞክሮ ወስደው የተሻለ የፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ማስቻል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የስቴም ማዕከል በአመታዊ ዕቅዱ መሠረት በተያዘው ሩብ ዓመት በገደብ ከተማ አስተዳደር ገደብ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በጮርሶ ወረዳ ቀዲዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በይርጋ ጨፌ አዳሜ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ከሳይንስ ክበብ አስተባባሪዎች እና ከሳይንስ መምህራኖች ጋር ውይይት በማድረግ ተማሪዎቻቸውን በፈጠራ ስራ እንዲያበረታቱ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መሰራቱን አቶ በፈቃዱ ገልፀዋል።
አቶ ትግሉ በቀለ፣ የጌዴኦ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ባለሙያ በበኩላቸው፤ በዚህ ዓመት በአስር ት/ቤቶች የሳይንስ ሳምንት እናከብራለን ብለን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል ጋር በጋራ በታቀደው መሰረት የተከናወነ መሆኑንና የተገኘው ውጤት ከተጠበቀው በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
በማሳያነት በ2014 ዓ.ም በይርጋጨፌ እና ሌሎች ት/ቤቶች ላይ የሳይንስ ሳምንት በተከበረበት ወቅት ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎችን ይዘው ቀርበው ማየታችን ውጤታማ መሆናችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ሳይንስና ቴክኖሎጂ የትውልድ ቋንቋ ነው ብለን በቅንጅት እየሰራን ነው ያሉት አቶ ትግሉ በክረምት፣ በቅዳሜና እሁድ መርሃ ግብር እንደዞናችን ከተለያዩ ት/ቤቶች ብዙ ተማሪዎችን ስቴም ማዕከል አስገብተን እያስተማርን ማዕከሉም እያሰለጠነ ተማሪዎቻችን የተሻለ የፈጠራ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነና ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ መሻሻሎችን እንዲሁም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ልጆቻችን የተሻለ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ያየንበት ነው ብለዋል፡፡
አቶ መብራቱ ኦብሴ፣ የይርጋ ጨፌ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፤ ይህ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራ በአሁኑ ሰዓት በየትምህርት ቤቱ እየተሰራ መሆኑንና በተማሪዎችም ዘንድ ትልቅ መነቃቃት እየፈጠረ መምጣቱን ገልጸው፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል እና የጌዴኦ ዞን እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የይርጋጨፌ ከተማ አዳሜ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው የ10ኛ ክፍል ተማሪ እንድሪያስ ደሳለኝ በሰጠን አስተያየት፤ በዚህ የሳይንስ ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፌ አዳዲስ ነገሮችን እንዳይ ረድቶኛል ሲል ገልጾልናል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ ከጌዴኦ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የየወረዳዎች ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ባለሙያዎች፣ የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *