Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 10/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ “ከስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ ደም መለገስ ነው” በሚል መሪ ቃል የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል የጤና እግር ኳስ ቡድን አባላት ደም የመሰብሰብ ዘመቻ አካሂደዋል።
አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የጤና ተግባር የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚፈልግ ስራ እንደመሆኑ የዛሬው የደም ልገሳ መርሃ ግብር በሆስፒታሉ የጤና እግር ኳስ ቡድን አስተባባሪነት ተከናውኗል።
ይህ የጤና ቡድን ምንም እንኳ ከተቋቋመ ከአስር አመት ያላነሰ ዕድሜ ቢያስቆጥርም በይበልጥ ግን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በልዩ ድጋፍ እንደ አዲስ እንደተደራጀ እና አሰልጣኝ ጭምር እንደተቀጠረለት ከዚሁ ጎን ለጎን በሆስፒታሉ ጤናማ የሆነ ሰራተኛ ለመፍጠር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ተገልጿል።
አቶ ትዝአለኝ አክለውም፤ ይህ የጤና ቡድን በከተማው ውስጥ የሚካሄዱ የተለያዩ የጤና ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ሆስፒታሉን ከማስጠራት ባለፈ እንደዚህ አይነት የደም ልገሳ፣ የአካባቢ ፅዳት፣ እንዲሁም የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ በንቃት በመሳተፍ የህክምና አገልግሎቶች በበጎ አድራጎት እንዲሰሩ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዲላ አጠቃላይ ሆስፒታል በርካታ እናቶች በወሊድ ምክንያት ደም እየፈሰሳቸው የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከአጎራባች ወረዳዎች እና ክልሎች ጭምር የሚመጡበት እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ድንገተኛ አደጋ የሚደርስባቸው ሰዎች የሚታከሙበት እንደመሆኑ አሁን ላይ በሆስፒታሉ ከፍተኛ የደም እጥረት ያለ ስለሆነ የጤና ቡድኑ ይህን ችግር ለመቅረፍ በዛሬው ዕለት ደም የመሰብሰብ ዘመቻ አዘጋጀቶ ደም በመሰብሰብ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ላደረገው በጎ ተግባር አቶ ትዝአለኝ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አቶ ምርቱ ተዘራ፣ በሆስፒታሉ የላብራቶሪ ባለሙያ እና የጤና እግር ኳስ ቡድኑ ሰብሳቢ በበኩላቸው፤ የጤና ቡድኑ ከተቋቋመ ረጅም ጊዜ እንዳስቆጠረ ገልጸው አባላቱ ኳስን ከመጫወትና ጤናቸውን ከመጠበቅ ባለፈ በከተማው የተለያዩ በጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሳተፍ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶችን በንቃት እየሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ምርቱ አክለውም፤ በዛሬው ዕለትም ቡድኑ ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር በሆስፒታሉ ይህን የደም ልገሳ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ እስከ መቶ ዩኒት ደም በመሰበብ በደም ዕጦት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ እናቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ መስራቱን ገልጸውልናል።
በመርሃ ግብሩ ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል የጥራትና ቁጥጥር ማሻሻያ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ሕይወት ታደሰ እና የ4ኛ አመት ተማሪ ተዘራሽ አበጀ፤ ደም መለገስ በደም እጦት ምክንያት ሳቢያ በወሊድና በተለያዩ አደጋዎች ምክንያት በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰውን ሞት ለመቀንስ እገዛው የላቀ እንደሆነ ገልጸው በዚህም በጎ ተግባር በመሳተፋቸው ከፍተኛ የሆነ የህሊና እርካታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል።
በቀጣይም ይህን መሰል የደም ልገሳ እና የጽዳት ዘመቻዎች በሌሎችም የዩኒቨርስቲው ግቢዎች ለማከናወን ፕሮግራም መያዙን ከአዘጋጆቹ ለማወቅ ችለናል።
በደም ልገሳው መርሀ ግብር የሆስፒታሉን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ሀኪሞች፣ አካዳሚክ ሰራተኞች፣ የጤና ቡድኑ አባላት፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት