የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የላብራቶሪ ኤግዚብሽን አካሄደ
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 05/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 2ተኛውን ሳምንት የላብራቶሪ ኤግዚብሽን አካሂዷል።
አቶ ዮናስ ተጠምቀ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ላብራቶሪዎች ከፍተኛ በጀት ወጥቶባቸው የተገነቡ እንደመሆናቸው መጠን አጠቃላይ የኮሌጁ መምህራንና የላብራቶሪ አሲስታንቶች ላብራቶሪዎችን በሚገባ ተጠቅመው ከመማር ማስተማሩ ባለፈ ለተቋሙ የገቢ ምንጭነትም ጭምር እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።