ለመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈጻሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ገለጻ ተሰጠ
ዲ.ዩ፡- ሐምሌ 2/2016ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ):- በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 3 እስከ 12/2016 ዓ.ም በበይነ መረብ እና በወረቀት ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ በዩኒቨርሲቲው በአስፈጻሚነት ለተመደቡ የፈተና ማዕከል ኃላፊ፣ የፈተና ጉድኝነት ማዕከል አስተባባሪ፣ የፈተና ጣቢያ ኃላፊና ሱፐርቫይዘሮች ስለ ፈተና አስፈጻሚዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም ስለተፈቀዱ እና ስለተከለከሉ ነገሮች በተመለከተ ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል።