ለአይነ-ስውራን ተማሪዎች በመሠረታዊ የኮምፒውተር እና የጆውስ ሶፍትዌር አጠቃቀም ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
ዲዩ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በድምፅ አማካኝነት በሚሰጥ ትዕዛዝ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል መሠረታዊ የኮምፒውተር እና የጆውስ ሶፍትዌር አጠቃቀም ዙሪያ ለአይነስውራን ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡