Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 17/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጠ የቡና ችግኞችን ከዱማርሶ ችግኝ ጣቢያ ለአርሶ አደሮች አሰራጭቷል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት፤ በእለቱ የመክፈቻ ንግግር አድርገው የቡና ችግኝ ስርጭቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ከዛሬ አምስት አመት በአካባቢው ተከስቶ የነበረው ውርጭ የአርሶ አደሩን ቡና አጥፍቶት ስለነበር በዛ መነሻነት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቡና ምርምር ስራ ገብቶ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተግባራትን እየፈጸመ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዶ/ር ችሮታው፤ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ጊዚያት የቡና ችግኞችን እያለማ ለአርሶአደሩ ከማሰራጨት ባሻገር አርሶ አደሩንም ሆነ ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን በዘርፉ እንዲሰማሩ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
አቶ ታጠቅ ዶሪ፣ የጌዴ ዞን ም/አስተዳዳርና የግብርና መምራያ ኃላፊ በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት እንደ ዞን የቡና ችግኝ መትከል በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን አንስተው፤ ዩኒቨርሲቲው ወቅቱን የጠበቀ በምርምር የታገዘ ምርትና ምርታማነቱ የተረጋገጠ የቡና ችግኝ አባዝቶ በነፃ ለአርሶ አደሮቻች ማደሉን አድንቀዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ በዘንድሮው የምርት ዘመን በአጠቃላይ በ5 ጣቢያዎች 442 ሺህ የቡና ችግኞች ለ816 አርሶ አደሮች ለማሰራጨት መታቀዱን ተናግረዋል። ከዚህም መካከል በዚህ የስርጭት መርሃ ግብር በይርጋጨፌ ዱማርሶ የችግኝ ጣቢያ 190 ሺህ ችግኞች ለ305 አርሶ አደሮች መሰራጨቱን ገልፀው በቀጣይ ቀናት ሌሎች ጣቢያዎች ላይ ያሉትም እንደሚሰራጩ ተናግረዋል።
በመርሃግብሩ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ዱላ ቶሌራ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የምር/ማህ/ጉድኝት ዋና ስራ አሰፈፃሚ ተወካይ፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉበትን አከባቢ ማህበረሰብ በምርምር ማገዝ አንዱ ተግባራቸው መሆኑን ገልፀው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ እየሰራ ያለው ስራ በሞዴልነት የሚያስጠቅስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በወቅቱ የቡና ችግኝ ሲወስዱ ያገኘናቸው አቶ ደሳለኝ ገመዴና አቶ ዳዊት ግዛው በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት ከወሰዱት የቡና ችግኝ ጥሩ ምርት እንዳገኙ ጠቅሰው ዘንድሮም ለዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በእለቱም ቡናቸው በማርጀቱና ምርታማነቱ በመቀነሱ ያረጁ የቡና ተክሎችን በመንቀል ከዩኒቨርስቲው ያገኙትን የቡና ችግኝ ለመትከል ማሳቸውን ባዘጋጁ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ የቡና ችግኝ ተከላ ተከናውኗል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et