Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲዩ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በድምፅ አማካኝነት በሚሰጥ ትዕዛዝ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል መሠረታዊ የኮምፒውተር እና የጆውስ ሶፍትዌር አጠቃቀም ዙሪያ ለአይነስውራን ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
አቶ ዮናስ ተጠምቀ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ ረዳት፤ በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር በመሠረታዊ የኮምፒውተር እና የጆውስ ሶፍትዌር ስልጠና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከጊዜው ጋር መራመድ እንዲችሉ ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ተመርቀው ሲወጡ በህይወታቸው ላይ በስራ ብቁ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
አቶ ዮናስ አክለውም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ከስር መሰረት ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቅ ተቋም መሆኑን ገልፀው ስልጠናውን የሰጡትን የማዕከሉ ኃላፊዎችና መምህራንን አመስግነዋል፡፡
አባቡ ተሾመ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክተር በበኩላቸው የመሰረታዊ የጆውስ ኮምፒውተር ስልጠና ፍላጎት ላላቸው የተቋሙ አይነስውራን ተማሪዎች መሆኑን ገልፀዉ በመማር ማስተማር ሂደት እንደ አቻ ጓደኞቻቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እና ጆውስ ሶፍትዌር አፕልኬሽን በመጠቀም የተለያዩ ለትምህርታቸው የሚያግዛቸውን የትምህርት መረጃዎች ማግኘት እንዲችሉ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ነው ብለዋል፡፡
ይህም ፍትሀዊ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንፃር ለተቋሙ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ደ/ር አባቡ አያይዘዉ ገልፀዋል።
አቶ ሰረቀ ብርሃን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህር እንደገለፁት ስልጠናው መሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎትን ማሳደጊያ ከኮምፒውተር ጋር ከመተዋወቅ ጀምሮ በተለይ አይነ-ስውራን ተማሪዎች ከጽሁፍ እና ከንባብ ጋር በተያያዘ መሰረታዊ ኮምፒዉተር እና የጆውስ ሶፍትዌር እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚያግዝ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል በሶሻል ሳይንስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ የሆነው ተማሪ አላዛር ኢያሱ የኮምፒውተር አጠቃቀም ባለማወቁ ለማንበብ እና ለመፃፍ የሰዎችን እገዛ ይፈልግ እንደነበር ገልፀዉ አሁን ግን ይህ ቴክኖሎጂ ብዙ ችግሮችን የሚያቃልልለት ስለሆነ ትልቅ ግብአት ያገኘበት ስልጠና እንደሆነ ተናግሯል፡፡
ስልጠናውን በትክክል ተከታትለው ለጨረሱ ሰልጣኞች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *