ዲ.ዩ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ 2016 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ይረዳል የተባለ የሞዴል ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል።
አቶ ዮናስ ተጠምቀ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ ረዳት እንደገለጹት፤ በሰኔ ወር ውስጥ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ ለዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ ተማሪዎች ምን ያህል እንደተዘጋጁ የራሳቸውን አቋም የሚፈትሹበት የሞዴል ፈተና ለተማሪዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸው፤ ቴክኒካል የሆኑ ከሶፍትዌርና ከኮምፒውተር ቅርበት ጋር ያለውን እንዲለማመዱ የሚረዳቸውና የሚያውቁበት ነው ብለዋል፡፡
ሄኖክ መኮንን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ልማት ኦፊሰር እና የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ተወካይ በበኩላቸው፤ ከዛሬ ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ለዋናው የመውጫ ፈተና የሚያዘጋጃቸውን በአጠቃላይ 2ሺ 356 ተማሪዎች ሞዴል ፈተና እየወሰዱ መሆኑን ገልጸው፤ እንደ መንግሥት የትኩረት አቅጣጫ መሠረት ኩረጃን በማስቀረት ብቃት ያለው ተማሪ ማውጣት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
አቶ በቀለ ወርቁ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አይ ሲቲ ዳይሬክተር፤ ለተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳቸው በተቋማችን መምህራን ፈተና መሰጠቱን ገልጸው፤ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በ Iexam ሲስተም ላይ መምህራኖቻቸው ቱቶሪያል ሲሰጡ እንደቆዩ እንዲሁም ማቴሪያሎችን ወደ Iexam ሲስተም ሲልኩ ቆይተው ፈተናውን እንዳዘጋጁ እንዲሁም ለመውጫ ፈተና ልምምድ ይረዳቸው ዘንድ ፈተናውን መሰጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et