Dilla University

News
Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 22/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት እና የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በጋራ የሚያከናውኑት የተቀናጀ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ልማት ፕሮጀክት (Enhancing Secondary Education in Gedeo Zone through comprehensive and professional support) ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የስራ ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሂዷል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር፤ በእውቀትና በክህሎት ያደገ ማሕበረሰብ ቴክኖሎጂ የመፍጠርና የመጠቀም አቅሙ ከፍ ያለ፣ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያምን፣ ህግንና ስርዓትን የሚያከብር፣ የአካባቢውን ፀጋ በውል ተገንዝቦ ጥቅም ላይ የሚያውል፣ የሀሳብ ልዩነትን የሚያከብር ዜጋ እንደሚፈጥር አብራርተው በሀገር ደረጃ የተጀመረውን የትምህርት ሪፎርም ለማገዝና በጌዴኦ ዞን ያለውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በመቀናጀት በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ውጤት መሠረት ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር መቀየር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መርሃ ግብሩን መጀመሩን ገልጸዋል።
ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማሕበረሰብ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየከወነ እንደሚገኝ አንስተው፤ በዞኑ በጊዜ ሂደት እየታየ የመጣውን የትምህርት ስብራት ተመራማሪዎች በመመደብና በመደገፍ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ግኝቱን ወደ ፕሮጀክት በመቀየር ወደ ተግባር በመግባቱ ደስ መሰኘታቸውን ገልጸው አመስግነዋል።
ዶ/ር ዝናቡ፤ አክለውም ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረግበት ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች፣ የጌዴኦ ዞን ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቱ የታሰበውን ዓላማ እንዲያሳካ ቀና ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አቶ ዘማች ክፍሌ የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ በአራት ዓመት ውስጥ 14.2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ይርጋጨፌ እና ገደብ ወረዳን ጨምሮ በአምስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጌዴኦ ዞን አስተዳደር፣ ከከተሞችና ወረዳ አስተዳደሮች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንደሚሆን አስረድተዋል።
መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፣ የምርምሩ ቡድን አባል በፕሮጀክቱ ይዘትና ምንነት ዙሪያ መነሻ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፤ በመድረኩ ሰፊ ውይይትና የሀሳብ ልውውጥ ተካሂዶ ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የየራሳቸውን ሚና ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በማስጀመሪያ መረሐ ግብሩ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች፣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር አመራሮች፣ በጌዴኦ ዞን የሚገኙ ወረዳዎችና ከተሞች አስተዳዳሪዎች፣ የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ አመራሮች፣ የወረዳዎችና ከተሞች ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et