Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 29/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በኢትዮጵያ የስቴም ፓወር ካንትሪ ዳይሬክተር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የስቴም ማዕከል ተገኝተው በማዕከሉ የተከናወኑ ተግባራትን ምልከታ አድርገዋል።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የተመራው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የኢትዮጵያ ስቴም ፓወር አባላት ቡድን በዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ምልከታ ያካሄደ ሲሆን በምልከታውም ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ የስቴም ፓወር ካንትሪ ዳይሬክተር በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ስቴም ማዕከል የተደረገው ምልከታ ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው ከስቴም ፓወሩ የተለያዩ እገዛዎችን ሲያገኝ ስለነበር በዛ መነሻነት እስካሁን በማዕከሉ የተሰሩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ለማየትና እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው በአገር አቀፍ ውድድሮች ያሸነፍንባቸውን የፈጠራ ስራዎች ለመመልከት ነው ሲሉ ተናግረዋ
በጉብኝቱ ወቅትም ካንትሪ ዳይሬክተሩ በማዕከሉ ያሉትን የግብአት ችግሮች በማሟላት እገዛ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ዶ/ር ችሮታው አያይዘው ገልጸዋል።
ዶ/ር ችሮታው አክለውም፤ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከስቴም ፓወር ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር የተሻሉ ተማሪዎችን በማፍራት በሀገሪቷ ቀጣይ ስራ ፈጣሪ ትውልድ ለመፍጠር እንደ ተቋም ትልቅ ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ስሜነህ ቀስቅስ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የስቴም ፓወር ካንትሪ ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የዛሬው ምልከታ በዋናነት በስቴም ማዕከሉ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ለማየትና ምናልባት እገዛ የሚፈልጉ ነገሮች ካሉም እዚህ ላይ እንደሚሰራ አንድ አካል እና ይህን ማዕከል እንዳቋቋመ እንደ አንድ ድርጅት ምን ላይ መርዳት እንችላለን የሚለውን ለመምከር እንደሆነ ገልጸዋል።
ካንትሪ ዳይሬክተሩ በምልከታቸውም፤ ማዕከሉ ጥሩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ መመልከታቸውንና ለዚህ ደግሞ በየዓመቱ ከዚህ ማዕከል የሚወጡ ልጆች በአገር አቀፍ ደረጃ ጭምር አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ መሆናቸው ለዚህ አንዱ ማሳያ ምስክር መሆኑን ተናግረዋል።
ይህን ማዕከል ከዚህ በተሻለ ቢደራጅ ምናልባትም ዞኑ ላይ በርካታ ልጆች ብዙ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን ይዘው መምጣት ይችላሉ ብለው እንደሚያምኑ አንስተዋል። እዚህ ላይ ለመስራት ከኃላፊዎች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ዶ/ር ስሜነህ አያይዘው ተናግረዋል።
ዶ/ር ስሜነህ አክለውም፤ በዲላ እና አካባቢው ያሉ የሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችም ይህ ትልቅ ማዕከል በአቅራቢያቸው መኖሩን አውቀው በክረምት እንዲሁም በቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብሮች መጥተው በመጠቀም በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች ላይ ያላቸውን ዕውቀት እንዲያዳብሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ከምልከታው የተገኙ ጠንካራና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ተነስተው የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደተሰጠባቸው ለማወቅ ተችሏል።