Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በቡና አዘገጃጀትና ጥራት ምርመራ ላይ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ ሕብረት ስራ ማሕበራት የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
አለሙ ደሳ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር በመርሀ ግብሩ ላይ ባሰሙት ንግግር፤ ዩኒቨርሲቲው በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ቡና የሚመረትበት አከባቢ የሚገኝ በመሆኑ ለቡና ልማት ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ስራዎች በመከወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው ቡና የሀገራችን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ለብዙ ሚሊዮን ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገቢ ምንጭ መሆኑን አንስተዋል።
ዶክተር አለሙ አያይዘውም፣ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በተደረገው የተልዕኮ ልየታ መሰረት በቡና ልማትና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ምርምሮችን በመስራት፣ በምርምር የለማ ቡና ለማሕበረሰብ በመስጠትና በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ፣ ስርዓተ ትምህርት በመቅረጽ በቡና መስክ ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራም በመክፈት፣ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠት፣ የቡና ምርምር የልህቀት ማዕከል ማደራጀትና ሌሎች ስራዎችን በመስራት የቡና ምርታማነት ጥራትን በመሻሻል ለአካባቢው ማሕበረሰብና ለአገር ጥቅም እንዲያስገኝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድቷል።
መምህር ብሩህ ተስፋሁን፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የአጫጭር ስልጠናዎች አስተባባሪ በበኩላቸው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለማሕበረሰቡ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች የቡና ልማት አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ በቡና ልማት ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሰጥ መቆየቱንና ይህን ስልጠናም በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ 28 የቡና ሕብረት ስራ ማሕበራት ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች በዘርፉ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው የዩኒቨርስቲው መምህራን በቡና አዘገጃጀትና ጥራት ምርመራ ሲሰጥ መቆየቱን እንዲሁም ስልጠናውን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚረዳቸውን ዕቅድ አዘጋጅተው በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቅንጅት የሚሰሩበትን የጋራ ስርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል።
ስልጠናውን ከሰጡ መምህራን መካከል መምህር እስማኤል ከሊል፣ በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የሆርቲካልቸር መምህርና በቡና ዘርፍ ተማራማሪ፤ ስልጠናው በአለም አቀፍ ደረጃ በጣዕሙ የሚታወቀውን የይርጋጨፌ የቡና እውቅናውን ጠብቆ እንዲዘልቅና ጥራት ያለውን የቡና ምርት ወደ ገበያ በማቅረብ አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚገባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ሥልጠናው ከቡና ችግኝ አዘገጃጀት ጀምሮ እስከ አፍልቶ መጠጣት ያለውን ሂደት የሸፈነ፤ የአካባቢውን ጥበቃ፣ የውሃ ብክለትና መፍትሔ፣ የገበያ ትስስርና የዓለም ቡና ገበያ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ያካተተ ጥሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን መምህር እስማኤል ከሊል ገልጸዋል።
ከሰልጣኞች መካከል አቶ ብርሀኑ ዋቆ እና አቶ ተስፋዬ ሚሊዲጋ በሰጡን አስተያየት፤ ስልጠናው ተግባር ተኮር፣ ከሙያቸውና ስራቸው ጋር የሚሄድ ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት ያገኙት መሆኑን ገልጸው፤ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለስራ ባልደረቦቻቸውና ለአርሶአደሮች በማካፈል ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ በማቅረብ አርሶአደሮች የልፋታቸውን ዋጋ እንዲያገኙ እንዲሁም አገራችን ከፍ ያለ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲዲላ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin