Dilla University

News
Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 27/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጌዴኦ ዞን መምሪያ፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳዎች ለተወጣጡ የሰላምና ፀጥታ ባለሙያዎች በሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሽብሩ ሚጁ እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም በተለይም ሀገር በቀል በሆነው የግጭት አፈታት ሂደት ላይ እንደ ዞን በሴክተሩ ላይ በደንብ ያለመስራት ክፍተቶች ስለነበሩ ክፍተቶች ለመሙላት እንደ መምሪያ በጠየቁት መሠረት ዩኒቨርሲቲው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ይህ ስልጠና በሰላም እሴት ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች መስጠቱን ገልጸዋል።
ኃላፊው አክለው፤ ይህ ስልጠና ለባለሙያዎች ከባህላዊ የግጭት አፈታት ሂደቶች ባለፈ፤ ግጭቶች ሲፈጠሩ አልያም ከመፈጠራቸው በፊት መንስኤዎችን በመለየት ከህዝቡ ጋር እንዴት መፍታት እንደሚቻል ለማየት ዕድል ጭምር የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ፈጠነ ባሌሲ፣ በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የስልጠናና ማማከር ኦፊሰር፤ ስልጠናው የጌዴኦ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ጽ/ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የዳሰሳ ጥናት ተደረጎ የጽ/ቤቱን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
ከአሰልጣኞች መካከል በዩኒቨርሲቲው በሀገረ-ሰብ ጥናት ተቋም ተመራማሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ገደቾ በበኩላቸው፤ ይህ ስልጥና በሰላም እሴት ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም በዘርፉ ላይ በሳይንስ ያገኙትን እውቀት ከሀገረ-ሰብ እውቀት ጋር አዋህደው ግጭቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲፈቱ ከማስቻሉም በላይ ሰልጣኞች በሳይንሳዊ እውቀቶች የማይፈቱትን ችግሮች በሀገረ- ሰብ እውቀቶች መፍታት እንዲችሉ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ተናግረዋል።
በስልጠናው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ስልጠናው የክህሎት እና የእውቀት ክፈተትን ለመሙላት የተሰጠ ስልጠና እንደመሆኑ መጠን፤ ባለሙያዎች ከስልጠና በኋላ ወደመጡበት ሲመለሱ በአጎራባች ቦታዎች እንደመኖራቸው በማህበረሰቡ ባህል የሚፈቱ ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳ የሀገረሰብ እወቀትን ጭምር ተጠቅመው የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በመጠበቅ ተጨባጭ ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል ከጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት የመጡት አቶ ሙሉጌታ ጠቀቦ እና አቶ ፍቃዱ ኢትቻ፤ ስልጠናው እስከዛሬ ከወሰዷቸው ስልጠናዎች የተለየ ዕውቀት ያገኙበት ስልጠና እንደነበር ገልጸው፤ በተለይ በሰላም እሴት ዙሪያ ላይ በባህል የሚፈቱ ችግሮችን በዕውቀት ጭምር እንዲፈቱ ትልቅ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በስልጠናው ከጌዴኦ ዞን፣ እንዲሁም ከምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የተውጣጡ ወደ 30 የሚጠጉ ባለሙያዎች ተሳታፊ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et