የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት የ30 ሚሊዮን ብር እና በርካታ ድጋፎችን አደረገ፡፡

ዲ.ዩ 21/2013 ዓ.ም (ህ.ግ) በሀገራችን ተቻችለን ተፈቃቅረን በፍቅር የምንኖር ህዝቦች ነን ያሉን ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዛሬ ለመቸገራችን ዋነኛው ምክንያት እርስ በርሳችን ፍቅር ማጣታችን ነው ብለውናል፡፡

ሀገር ስትደፈር ብሔር፣ ሃይማኖት ቀለም ሳይለየው በዘመናዊ መሳሪያ የመጣውን ጣልያንን ድል የነሳው በቂ ትጥቅ ሳይኖር በፍቅርና በሀገር ወዳድነት የተነሳ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ይህን የተረዳው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ከበጀቱ 2 ሚሊዮን በማውጣትና አባላቱም ደግሞ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል የገቡ መሆኑንም ዶ/ር ዳዊት ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሠራዊቱ ለሀገራችን ደሙንና አጥንቱን ሲሰጥ እኛ ደግሞ ከጎኑ በመሆን አለኝታነታችንን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለው የዲላ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት የወሰኑ ሲሆን ይህም በእውነቱ ሠራተኛው ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ክብር ያሳያል ብለዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ካፒታል በጀት÷ ከማኔጅመንቱ አባላትና ከሠራተኛው የሚዋጣው በአጠቃላይ 30 ሚሊዮን በላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከገንዘብ ድጋፉ ጎን ለጎን የደም ልገሳ መሪሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለዚህ ጀግና ሠራዊት አብሮነቱን በተግባር አሳይታል::

በተጨማሪም በሪፌራል ሆስፒታልና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚሰሩ ሰራተኞችም በአካል በመጓዝ ሙያዊ አስተወጽኦ ለማበርከት ያመለከቱትን የኮሌጁ የሂደቱ ግብረ-ሃይል አስተባባሪዎች እየመዘገቧቸው እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡

ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎችም መካከል አቶ ወርቃገኘው በፍቃዱ በበኩላቸው ይህ ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረው በአሁን ወቅት የወር ደመወዝ ለመስጠት ቃል ገብተው በተጨማሪም በግላቸው አንድ በሬ /ሰንጋ/ ለሠራዊቱ አጋርነታቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የወር ደመወዝ ከመለገስ ባለፈ በተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፋቸውን እንደምቀጥሉ ተናግረዋል፡፡