የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከUNHCR ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ያዘጋጀው ስልጠና በይርጋጨፌ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

ዲ.ዩ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግና አስተዳደር ጥናቶች ኮሌጅ ከUNHCR ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሠረታዊ መብት እና የሀገራት ግዴታ ዙሪያ በይርጋጨፌ ከተማ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ እንግዶችና ባለድርሻ አካላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግና አስተዳደር ጥናቶች ኮሌጅ በምርምር ዘርፍ ምክትል ዲን አቶ ተካልኝ ዱጌ ስልጠናው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት እንደሆነ ገልጸው በስልጠናውም የተፈናቃዮች መብቶች ምንድ ናቸው? የመንግስታትስ ግዴታስ ምንድነው? ተቋማትስ ለተጎጆዎች የሚያደርጉት ክትትልና ድጋፍ ምን መምሰል አለበት? የሚሉ ሃሳቦችን በስፋት ለማንሳትና ለችግሮቹም በጋራ መፍትሔ ለመስጠት እንደታሰበ ገልጸዋል።
ስልጠናው ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት በይርጋጨፌ፣ በገደብ እና በዲላ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን በስልጠናውም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል።