ዲላ ዩኒቨርሲቲ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ
ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአራቱም ግቢዎች ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል፡፡
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል እንደ ሀገር እቅድ ተይዞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በአራቱም ግቢዎች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራ ማከናዎናቸውን ገልጸዋል።