ዲላ ዩኒቨርሲቲ 434 ተማሪዎችን በነገው እለት ያስመርቃል
ዲ.ዩ:- የካቲት 15 /2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ):- ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስምራቸው የቆዩ 434 ተማሪዎችን በነገው እለት ያስመርቃል። የዩኒቨርሲተው ሴኔት ጉባዔ በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ የእጩ ምሩቅ ተማሪዎችን ውጤት አጽድቋል።
ዲ.ዩ:- የካቲት 15 /2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ):- ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስምራቸው የቆዩ 434 ተማሪዎችን በነገው እለት ያስመርቃል። የዩኒቨርሲተው ሴኔት ጉባዔ በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ የእጩ ምሩቅ ተማሪዎችን ውጤት አጽድቋል።
ዲ.ዩ፤ 14/06/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በተለያዩ የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብሮች ያስፈተናቸው ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሁኗል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 13/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎችና በመሰረታዊ የቤተ ሙከራ ጥራት አተገባበር ዙሪያ ከይርጋጨፌ፣ ቡሌና ገደብ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ለተውጣጡ የጤናና የሕክምና ቤተ ሙከራ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ተገልጿል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና በምርምር፣ ህትመት፣ ሥነ ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው በተመደበላቸው በጀት የሚሰሩ ምርምሮች 13ኛው ዓመታዊ የምርምር ቫሊዴሽን እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዲ.ዩ፤ የካቲት 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ ከየካቲት 06 -11/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 06/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ከየካቲት 6 -11 የሚሰጠውን አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 03/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የስፔኑ የካታሎኒያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ልማት በስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 02/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ)፦ “ሆፕ ወክስ” (HOPE WALKS) በጎ አድራጎት ድርጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት እግራቸው ቆልማማ በሆነ ታካሚዎች ዙሪያ ከጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ለተወጣጡ 100 ለሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን በሆስፒታሉ ቆልማማ እግር ላላቸው ታካሚ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ዶ/ር ችሮታው አየለ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልቦና ውቅር ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ከቡና ጋር የተያያዙ ችግሮችን በምርምር መፍታት እንደሚገባ የገለጹት።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 1/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በትብብር ያዘጋጁት “ክብር ለአካባቢ ጥበቃ ጀግኖቻችን የጌዴኦ ማሕበረሰብ” በሚል መሪ ቃል የጌዴኦ ብሔር የቋንቋና ባህል- ዳራሮ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።