አይ.ሲ.ቲ መሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማጠናከሪያ ሥራ

በአይ.ሲ.ቲ መሠረተ ልማት የማስፋፊያና ማጠናከሪያ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ለመሠረተ ልማቱ መስፋፋት ዩኒቨርሲቲው ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡
ዲዩ፤ መስከረም 9 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአይ.ሲ.ቲ መሠረተ ልማት የማስፋፊያ፣ ማጠናከሪያና ማሻሸያ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ኢንፎረሜሸንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ፊልጶስ ገልጸዋል፡፡
የማሰፋፊያ ፕሮጀክቱ በደህንነት ካሜራ፣በገመድ አልባ ኔትወርክ እና በዳታ ማዕከል መሠረተ ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑን የገልጹት ዳይሬክተሩ የመሠረተ ልማቶቹ መስፋፋት ለመማር ማስተማሩም ሆነ ለደህንነቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አንስተዋል፡፡
የደህንነት ካሜራዎች ዘመናዊና የ2019 እና የ2020 ሞዴሎችና ብዛት ያላቸው ካሜራዎች በሁሉም አቅጣጫ ጥራት መቅረጽ የሚችሉ መሆናቸውን አቶ ተመስገን ያነሱ ሲሆን የግቢዎችንም ደህንነት በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያበረክቱና ሁሉንም ካሜራዎች መቆጣጠሪያ ክፍልም እንዳለው አብራርተዋል፡፡
ገመድ አልባው የኔትወርክ ዝርጋታ ከዚህ በፊት ከነበረው አነስተኛ ተደራሽነት በከፍተኛ ሁኔታ በማሻሻ መምህራንና ተማሪዎችን የሚያገለግል ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን የተደራሽነት ችግር በተሸለ ሁኔታ እንደሚቀርፍ አቶ ተመስገን ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ እነዚህን አይ.ሲቲን መሠረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማጠናቀቅ ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ ዩኒቨርሲቲው ወጪ ያደረገ ሲሆን ከመሰከረም 30 ጀምሮ የደህንነት ካሜራዎችና የገመድ አልባ የኢተርኔት መሥርመሮች አገልግሎት መሥጠት እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡