የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች በካምፓስ ሕይወት አኗኗር ጥበብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ::

ዲ ዩ ሐምሌ 3/2013(ህ.ግ.) ወደ ዩኒቨርስቲያችን ተመድበው የመጡትን ተማሪዎች ተቋሙም ሆነ ክፍሎች ለመቀበል ያደረጉትን ዝግጅት በመግለፅ እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኤች አይ ቪ መ/መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ሽፈራዉ ወደ መማር ማስተማር ስራ ከመገባቱ በፊት የካምፓስ ህይወት የመምራትን ጥበብ ግንዛቤ እየተዝናኑ እውቀት እንዲቀስሙ ታሰቦ የተዘጋጀ መደረክ ነው ብለዋል::
በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ግንዛቤ ካስጨበጡት መካከል በካውስልንግ የረዥም አመታት ልምድ ያላቸው የስነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህር ዶ/ር ታረቀኝ ታደሰ ተማሪዎች በተቋም ቆይታቸው ወቅት እንዴት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ግንዛቤ ያስጨበጡ ሲሆን ከሕይወት ተሞክሮአቸውም አካፍለዋል::
የዲኬት ኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስነ ተዋልዶ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ገበየሁ በበኩላቸው ተማሪዎች በተቋም በሚቆዩበት ወቅት ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ስራዎችን በዕቅድ የመምራትን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰተው አንስተዋል::
በተጨማር የዜሮ ኘላን አባላት ሰለክበቡ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በእለቱ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል አዝናኝ ጡመ ዜማ በማቅረብ አዲስ ተማሪዎችን ማዝናናቱን መረዳት ችለናል::