የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቡና ልማት ላይ ስልጠና ለመስጠት ለግብርና ባለሙያዎች አቀባበል አደረገ፡፡

ዲዩ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከኢሊባቡር ዞን ለተወጣጡ 39 የግብርና ባለሙያዎች በቡና ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለሁለት ወር የሚቆይ ስልጠና ለመስጠት ለሰልጣኞች አቀባበል አድርጓል፡፡
በአቀባበሉ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በምርምር ላይ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን በአርሶአደሩ ዙሪያ መልካም ልምዶችን ለማስፋትና የቡና ሴክተሩ ራሱን ችሎ በተሻለ ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ይህን መሰል ስልጠና መሰጠቱ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቡና ምርምር ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አለሙ ደሳ በበኩላቸው ይህ ስልጠና ሰልጣኞቻችን ተገብውን ዕውቀት ይዘው በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲያመጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡