የዩኒቨርሲቲው ካውንስል የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የ800,000 ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ዲ/ዩ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) በዩኒቨርሲቲው ካውንስል የተደረገው የ800,000 ብር ድጋፍ ሴት ተማሪዎችን ውጤታማ እና ስኬታማ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ድጋፍ እንደሆነ የገለፁት የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለም ብርሃኑ ይህ ድጋፍ ለንጽህና መጠበቂያ እና ለመማሪያ ቁሳቁስ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ አለም አያይዘውም የዚህን መሰል ድጋፍ ባለፉት ጊዜያትም የዩኒቨርሲቲው ካውንስል እያደረገ እንደመጣ ገልፀው ድጋፉ የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎችን በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ ተማሪዎቹ በተቋሙ ላይ ያላቸውን እምነትና አጋርነት የሚጨምር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን ሲቀበሉ ካገኘናቸው ተማሪዎች መካከል ተማሪ በእምነት ሽመልስና ተማሪ ናርዶስ ግሩም እንደገለፁልን በኢኮኖሚ አነስተኛ ደረጃ ላሉ ሴት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ይህን መሰል ድጋፍ መደረጉ ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲከታተሉ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡