የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቡና ምርት ልማትና ዝግጅት ያሰለጠናቸውን የግብርና ባለሙያዎች ሊያስመርቅ ነው፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም (ህ.ግ) ስልጠናው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከGIZ ኢትዮጵያ አቅም ግንባታ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከኢሊባቡር ዞንና ወረዳዎች ለመጡ 38 የግብርና ባለሙያዎች በቡና አመራረትና ልማት ዙሪያ ሲሰጥ የቆዬ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን የምረቃ ሰነ-ስርዓቱም ቅዳሜ ነሐሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ (MPH) ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በድምቀት ይካሄዳል፡፡
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የፌዴራል ቡና እና ሻይ ዋና ባለስልጣን፣ የGIZ ኢትዮጵያ ተወካይ÷ ለስልጠናው አስተዋፅኦ ያደረጉ ባለድርሻ አካላት÷ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች÷ የዩንቨርስቲው አመራሮች እና ሠራተኞች ይገኙበታል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በቡና ልማት ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በ2014 ዓ.ም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስና ምጣኔ (MSc in Coffe Science & Economics) የድህረ-ምረቃ ትምህርት ለመጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን በፕሮግራሙም ከነሐሴ 10/2013 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 03/2013 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚያካሂድ የቡና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ዓለሙ ዴሳ ገልፀዋል፡፡