የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በቡታጅራ ባዘጋጀው ፎረም ለዶ/ር ሰላማዊት አየለ በስራ ዘመን በአመራር ብቃት የላቀ የአመራር ዘርፍ ሽልማት ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ ነሐሴ 28/2013 ዓ.ም (ህ.ግ.) በቡታጅራ በተካሄደው የደቡብ ክልል ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የጤና ሴክተር የ2013 ዓ.ም በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም የምክክር መድረክ ላይ በተደረገው የእውቅና መድረክ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፈራል ሆስፒታል ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰላማዊት አየለ በስራ ዘመናቸው በላቀ አመራር ዘርፍ በአመራር ብቃት እና በትልቅ ትጋት ቁርጠኝነት ለብዙዎች አርአያ በመሆን ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት የክልሉ ጤና ቢሮ እውቅናና ሰርተፍኬት ክርስታል ዋንጫ መሸለማቸው ተገለፀ፡፡
በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ወ/ሮ ቀመሪያ ረሽድ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ማህበራዊ ዘርፍ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በበኩላቸው ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ራሳቸውን ለተቋማቸው በመስጠት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣታቸው ነው ብለዋል፡፡
ሽልማቱ አሁን እየሰራሁ ላለሁትና በቀጣይ ልሰራ ላቀድኩት ስራዎች ትልቅ ጉልበትና ብርታት ይሆነኛል ያሉት ዶ/ር ሰላማዊት የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ከመጣር ባለፈ ይህን ሽልማት አገኛለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም ነበር ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሰላማዊት አየለ እንኳን ደስ አለዎት!
እንኳን ደስ አለን!