የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል አመራሮችና ሠራተኞች አዲሱን ዓመት በበጎ ፍቃድ ስራ መቀበላቸው ተገለፀ::

ዲ.ዩ መስከረም 02/2014 ዓም (ህ.ግ) ትልቁ ደስታና ዕርካታ የሰው ልጅን በመርዳት የሚገኘውን ውጤት ማየት ነው ያሉን ዶክተር ሰላማዊት አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ም/ኘሬዝዳንት መላውን ሠራተኛ እንኳን ለ2014 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ ብለው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሠራተኞች ከበጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችና ተቋማት ጋር በመተባበር አዲሱን አመት በአዲስ ራዕይና በአዲስ ተግባር መጀመራቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል:: 

የአዲሱ ዓመት ክብረ በዓል ከታካሚዎች÷ ከጎዳና ልጆችና ከአቅመ ደካማ እናቶችና አባቶች ጋር በመሆን በሆስፒታል ቅጥር ግቢ የተከበረ ሲሆን በዕለቱም የተዘጋጀውን ማዕድ በጋራ በመቋደስና ለጎዳና ልጆች ከበጎ ፍቃደኞች የተሰበሰበውን ልብስ በማደል ተከብሮ መዋሉን ዶ/ር ሰላማዊት ገልፀዋል:: 

እንዲህ አይነት ተግባር በጥራትና ቁጥጥር ማሻሻያ  ጽ/ቤት ከሚሰሩ የጥራት ለውጥ ሥራዎች አንዱ የሆነው የራህራሄና አክብሮት ህክምና (CRC) አገልግሎት አካል ነው ብለዋል:: 

በተያያዘም የማህበረሰብ አገልግሎት ከማጠናከር አኳያ "ተስፋ የበጎ አድራጎት ማህበር (Hope Charity)" አቋቁመው ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል: