የዲላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ አሰራርና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠናና ምክክር መድረክ አደረገ፡፡

ዲ.ዩ መስከረም 13/2014 ዓ.ም (ህ.ግ) ሀገር ልታድግና ወደ አለመችበት ደረጃ ልትደርስ የምትችለው ያላትን ሀብትና ንብረት በአግባቡ ስትጠቀም ነው ያሉን ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ በዩኒቨርሲቲው ያሉ የፋይናንስ፣ የግዥ፣ የኦዲት፣ የዕቅድና የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን ስልጠና መስጠት ያስፈለገው በሦስቱም ግቢዎች ያልተማከለ አሰራር ለመዘርጋት የሚደረግውን ጥረት ለማሳለጥ ነው ብለዋል፡፡
በዋናነት አሉ ዶ/ር ዳዊት በሦስቱም ግቢዎች በጄጂ የተመደቡ ሰራተኞችን ከነባር ሰራተኞች ጋር በስራ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና የሦስቱም ግቢዎች አሰራር አንድ ወጥ እንዲሆን ታስቦ ነው ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስልጠናው ከመንግስት ሊወርድ በተዘጋጀው የዲጂታል ትራንዛክሽን ላይ ሰራተኛው በቂ እውቀት ይዞ ውጤታማ በመሆን ተገልጋዩን እንዲያረካ እንዲያስችል ነው ብለዋል፡፡
አቶ ታምራት ታደሰ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት ዳይሬክተር በበኩላቸው ይህ ስልጠና የሰራተኛውን አቅም ከማጎልበቱ በዘለለ እርስ በራሳቸው እንዲተዋወቁና በተቋሙ የሚኖረውን የፋይናንስ አሰራር ዘመናዊና ወጥ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል፡፡
አቶ ታምራት በቀጣይ ማናቸውም ክፍያዎች ኤሌክትሮንክ ስለሚሆኑ ሰራተኛው ይህን አሰራር ቀድሞ በማወቅ እንዲዘጋጅ ያስችለዋል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ሲሰለጥኑ ያገኘናቸው አቶ ጌታቸው እቲሶ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክተር እና አቶ ወርቅአገኘሁ በፍቃዱ የኦዳያአ ግቢ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የዚህ አይነት ስልጠና በክፍሉ መሰጠቱን አመስግነው ስልጠናው ተቋሙ በውስጥ ኦዲትን ሆነ የተለያዩ አሰራሮችን የሚያዘምን በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡