የዲላ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማዕከል (ECDD) ጋር በመተባበር ለአይነ ስውራን ተማሪዎች በውጤታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በጃውስ የታገዘ የኮምፒውተር ስልጠና ሰጠ፡፡

ዲ.ዩ. ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ.) የአካዳሚ ጉዳዮች ም/ኘሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነዲ ገቢሳ እናንተ መምህራን በመሆናችሁ ይህ አሁን ላይ የወሰዳችሁት መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ለስራችሁ ትልቅ እገዛ አለው ብለው የኮምፒውተር ዕውቀት በስልጠና ብቻ የሚገኝ ሳይሆን እለት ተእለት በሚደረግ ልምምድ የሚጎለብት በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥበት አሳስበዋል፡፡
እድሉ ከተሰጣቸው አይነ ስውራን ከማንኛውም የተሻለ ብቃትና ክህሎት እንዳላቸው ስለሚያምን እኔ አልገረምም ያሉን ደግሞ የትምህርትና ስነ-ባህሪ እንስቲትዩት ዲን ዶክተር መስፍን ሞላ ከዚህ በፊት የኔ መምህር የነበሩት የብዙ ሙያዎች ባለቤት እንደነበሩ አውስተው ለብዙዎች ውጤታማትም አርዓያ ነበሩ ብለዋል፡፡
ተማሪዎቻችን በመደበኛው መርሃ ግብረግብር መምህራን ናቸው ያሉን የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር አባቡ ተሾሜ መሰረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት መቅሰማችሁ አለም በአሁኑ ሰዓት የመረጃ መተላለፍያው የዘመነ በመሆኑ ለእናንተ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ሰልጠናውን ሰልጥነው ከተመረቁ መካከል ደግሰው ሌጮ ከሀዲያ ዞን የመጣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የእንክሉሲፍ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሲሆን ያገኘው ዕውቀት ለስራው ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብሎናል፡፡